Tender Detail

Tender Details


ብርሃን ባንክ አ.ማ. ታዳሽ የሃይል ምንጭ አማራጮችን የመጠቀም ስትራቴጂ ይዞ እየተገበረ ይገኛል፡፡ በዚሁ መሰረት ሲጠቀምባቸዉ የነበሩ ባለ 20 KVA ያገለገሉ ‘PERKINS’ ‘AKSA’ ‘CGM’ እና ‘LISTER’  ጀነሬተሮችን ለማንኛዉም ግለሰብ ወይም ድርጅት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡


ያገለገሉ ጀነሬተሮች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁ. ብ/ባ/ፕ/ማ/ሎ-10/18

ብርሃን ባንክ አ.ማ. ታዳሽ የሃይል ምንጭ አማራጮችን የመጠቀም ስትራቴጂ ይዞ እየተገበረ ይገኛል፡፡ በዚሁ መሰረት ሲጠቀምባቸዉ የነበሩ ባለ 20 KVA ያገለገሉ ‘PERKINS’ ‘AKSA’ ‘CGM’ እና ‘LISTER’  ጀነሬተሮችን ለማንኛዉም ግለሰብ ወይም ድርጅት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

 

  1. ተጨራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ያገለገሉ ጀነሬተሮች፤ ዝርዝራቸዉ፣ ብዛታቸዉ፣ የጨረታ መነሻ ዋጋቸዉ ለጨረታዉ በተዘጋጀዉ ሰነድ በዝርዝር ተቀምጧል፡፡
  2. ለጨረታ የቀረቡት ያገለገሉ ጀነሬተሮች የሚገኙት ገላን ከተማ ቱሉ ጉራቻ ቀበሌ ኢንዱስትሪ መንደር በሚገኘዉ የባንኩ መጋዘን ሲሆን፣ ከታች በ9ነኛ ተራ ቁጥር በተጠቀሱት ስልክ ቀጠሮች በቅድሚያ ደዉለዉ ቀጠሮ በማስያዝ ማየት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በማንኛዉም የብርሃን ባንክ ቅርንጫፍ ክፍያ ፈፅመዉ ደረሰኙን በማቅረብ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት የቀድሞዉ ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ከነበረበት ቦታ ፊት ለፊት ከሚገኘዉ ወመሳድኮ ግቢ 2ተኛ ፎቅ ከፕሮፐርቲ ማኔጅመንት እና ሎጂስቲክስ አስተዳደር ቢሮ ለጨረታዉ የተዘጋጀዉን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በዝርዝር በተገለፀዉ መሰረት ለሚጫረቱበት ጀነሬተር የተጠቀሰዉን የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ 10% ለእያንዳንዱ ጀነሬተር በተናጠል በብርሃን ባንክ ስም የተዘጋጀ C.P.O. ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ያገለገሉ፤ ጀኔሬተሮች የሚገዙበትን ዋጋ በተዘጋጀዉ የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም ላይ በመሙላት ከጨረታ ማስከበሪያ P.O ጋር፣ በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት የቀድሞዉ ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ከነበረበት ቦታ ፊት ለፊት በሚገኘዉ ወመሳድኮ ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ፕሮፐርቲ ማኔጅመንት እና ሎጂስቲክስ አስተዳደር ቢሮ ለጨረታዉ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡
  6. ጨረታዉ ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸዉን ባስገቡበት፣ በ5ተኛ ተራ ቁጥር በተጠቀሰዉ አድራሻ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀንና ሰዓት ባይገኙ በሌሉበት ይከፈታል፡፡

 

  1. ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑበትን ጀነሬተር/ጀነሬተሮች ያሸነፉበትን ዋጋ አጠቃለዉ በመክፈል አሸናፊነታቸዉ በተገለፀላቸዉ በ10 ቀናት ዉስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህን ሳያደርጉ ቢቀር ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል፡፡
  2. ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ ሊሰርዝ ይችላል፡፡
  3. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፣ 0918890721 / 0998411523 / 0114437439 / 0116631729 ይደዉሉ፡፡
Save Tender