Tender Detail

Tender Details

  • Company Abyssinia Bank
  • Address , Phone: +251-115584271
  • Website
  • Deadline21 May 2026, 3:30 AM
  • magazineReporter Tenders
  • Bid Document Price
  • opening date2026-05-21 04:00:00
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure

አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን እና በሠንጠረዡ ውስጥ የተመለከተውን ተሽከርካሪ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 መሠረት ንብረቱ ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን እና በሠንጠረዡ ውስጥ የተመለከተውን ተሽከርካሪ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 መሠረት ንብረቱ ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

  • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
  • የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
  • ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀን እና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
  • የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል።
  • ንብረቱን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል።
  • በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ/ ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
  • የጨረታ ቦታ አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 7 ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት 4 ፎቅ ህንፃ B ላይ በሚገኘው የፎርክሎዠር እና ዴት ሊቲጌሽን ዲቪዥን የጨረታ ክፍል ውስጥ ነው።
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115 15 11 53 እና 0115 15 07 11 አ.አ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
  • ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የተበዳሪው ስም
የመያዣ ሰጪው ስም
የሰሌዳ ቁጥር
የተሸከርካሪው ዓይነት እና የተሰራበት ዘመን
የተሸከርካሪው ሞዴል
የሻንሲ ቁጥር
የሞተር ቁጥር
የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር
ጨረታዉ የሚካሄድበት ቀን
የምዝገባ ሰዓት
የጨረታ ሰዓት
አቶ ተሾመ ዮሀንስ ኡሳሞ
ተበዳሪው
ኢት-03-A23181
የጭነት – ቻይና ሲኖ ትራክ፣ 2021 (እ.ኤ.አ)
ZZ1257S4341W

 

LZZ5BLSF9MA868405
WD615.47*210407015937*
7,932,125.00
 

ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም

 

8፡30- 9፡30

 

9፡30-10፡00

 

Save Tender