የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለብድር ገንዘብ ማካካሻነት በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 መሰረት በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከበውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን የመያዣ ንብረቶች በልዩ ድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለብድር ገንዘብ ማካካሻነት በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 መሰረት በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከበውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን የመያዣ ንብረቶች በልዩ ድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
ተ.ቁ |
የተበዳሪው/ የመያዣ ሰጪው ስም |
የንብረትአድራሻ |
የንብረት ዝርዝር |
የቦታ ስፋት (በሄክታር) |
የጨረታ መነሻ ዋጋ (በብር) |
የጨረታሁኔታ |
የጨረታ ደረጃ |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
1 |
አቶ ግርማ አፈወርቅ መድምም |
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንፋስ ስ/ላ/ ክ/ከተማ ወረዳ 08 |
ጋቴፕሮ ቆርቆሮ ፋብሪካ፤ የህንፃ ግንባታዎች፣የኤልክትሪክ ስራዎች፣ ማሽነሪዎች፣ ቁሳቁሶች፣የቢሮ ዕቃዎችና መገልገያዎች፣ የጥሬ ዕቃና የምርት ክምችት |
1,678 ከሬ ሜትር በሊዝ የተገኘ መሬት |
122,600,997.28 (አንድ መቶ ሃያ ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሰባት ብር ከሃያ ስምንት ሳንቲም) |
ልዩ ድርድር |
አንደኛ |
ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋት 4፡00-6፡00 ሰዓት |
ማሳሰቢያ፤
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመግዛት ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ፣ ስምና አድራሻቸውን በፎርማቱ ላይ በመጥቀስ በባንኩ ዋና መ/ቤት ሁለተኛ ታወር ምድር ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሣጥን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣ ከሦስተኛው ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ሆኖ ከጠዋቱ 3፡50 ሰዓት ድረስ በማስገባት ከ4፡00-6፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ ቀርበው መደራደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ባንኩ ያስያዘውን ገንዘብ ይወርሳል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰንጠረዡ በተመለከተው ቀንና ሰዓት በባንኩ ዋናው መ/ቤት ታወር ሁለት 5ኛ ፎቅ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ ህጋዊ ሰውነት ያላቸው አካላትን ወክሎ በጨረታው ለመሳተፍ የሚቀርብ ሰው የማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ/መተዳደሪያ ደንብ ከእነ ማሻሻያዎቹ (ካለ)፣ የንግድ ምዝገባ፣ የንግድ ፍቃድ፣ ሌሎች አስፈላጊ ማስረጃዎችን እና የተረጋገጠ የውክልና ስልጣን ሰነዶችን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- 15% የተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው ይከፍላል፡፡
- አንዳንድ የድርጅቶች ንብረቶች የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው ስለሆኑ ገዢው የቀረጥ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥ፤ታክስ ለመክፈል ይገደዳል፡፡
- ተጫራቾች ንብረቱን ለመጎብኘት ከፈለጉ አስቀድሞ ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በመያዝ ንብረቱን መጎብኘት ይችላሉ፡፡
- ባንኩ ንብረቱን የሚሸጠው ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ይሆናል፡፡
- የንብረቱ ስመ-ንብረት ለገዥው እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ያሳወቃል:: ገዥው ጉዳዩን ተከታትሎ የማስፈፀም ሃላፊነት አለበት፡፡
- በጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ናቸው፡፡
- በጨረታው ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋና መ/ቤት ታወር ሁለት ሦስተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኦንጎይንግ ኮንሰርን ፕሮጀክትስ እና አኳየርድ አሴትስ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011–524-53-73/011-524-42-69 ደውሎ ማግኘት ይቻላል፡፡ የመያዣ ንብረቶቹን መጐብኘት የሚፈልግ ከዳይሬክቶሬቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጐብኘት ይቻላል፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
