Tender Detail

Tender Details

  • Company ለመጽደቅ የዘለቄታ በጎ አድራጎት ድርጅት
  • Address አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ, Phone: +251976572397
  • Website
  • Deadline27 May 2026, 2:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2026-05-18 14:00:00
  • Categories Water Well Drilling , Drilling

ለመጽደቅ የዘለቄታ በጎ አድራጎት ድርጅት የጥልቅ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ /Deep Well Drilling Project/ ተቋራጮችን ለማሰራት ይፈልጋል


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጥልቅ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ / Deep Well Drilling Project/

ቦታ፦ በደብረ ብርሃን እምዬ ምኒሊክ ክፍለ ከተማ ፣ ሎሬት አፈወርቅ ተክሌ ቀበሌ፣ ቦራሌ ቱሉ አምባ እና ጠንቆሌ የገጠር ንዑስ ቀበሌ።

ለመጽደቅ የዘለቄታ በጎ አድራጎት ድርጅት በደብረ ብርሃን ዙሪያ በሚገኙ 4 የፕሮጀክት ሳይቶች ላይ የ4 ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች ቁፋሮ፣ ግንባታ እና የውሃ ምርታማነት ሙከራ ሥራዎችን ብቃት ባላቸው ተቋራጮች ለማሰራት ይፈልጋል።

v  ለመፅደቅ ሳይት፦ 1 ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ (ከ160-180 ሜትር)።

v  የቦራሌ፣ የጠንቆሌ እና የቱሉ አምባ መንደሮች፦ 3 ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች (ከ140-160 ሜትር)።

ተጫራቾች ሊያሟላቸው የሚገቡ መስፈርቶች፦ ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የሚከተሉትን ሕጋዊ ማስረጃዎች ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

v  የዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የዘመኑ የግብር ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰነድ።

v  ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ወይም ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የደረጃ 5 (WWC/WWD-5) እና ከዚያ በላይ የሆነ የብቃት ማረጋገጫ ምስከር ወረቀት።

v  በመንግሥት የጨረታ እገዳ (Debarment) ውስጥ ያልተካተቱ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ።

v  ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከተለቀቀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 13 ተከታታይ የሥራ ቀናት (ቅዳሜን ጨምሮ ) ዘወትር በሥራ ሰዓት መተው የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ) የኢትዮጵያ ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

v  ተጫራቾች የቴክኒክ እና የፋይናንስ ሰነዶቻቸውን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ (አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

v  ጨረታው በ13ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ በ8:00 ሰዓት ታሽጎ፣ በዚያው ቀን በ8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ ፡ አያት ዞን አምስት መንገድ 14 

+251 97 657 2397/ +251 91 361 0673

tojustify24@gmail.com / info@alemetsdek.com 

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

 

ለመጽደቅ የዘለቄታ በጎ አድራጎት ድርጅት

Save Tender