ኦሮሚያ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለሰጠው ብድር በዋሰትና የያዘዉን በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የሐራጅ ማስታወቂያ
ኦሮሚያ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለሰጠው ብድር በዋሰትና የያዘዉን በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
| ተ.ቁ | የተበዳሪው ስም
|
የንብረት አስያዥ ስም | ለጨረታ የቀረበው ንብረት ዓይነት | አበዳሪው ቅርንጫፍ | ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻና የቦታ ስፋት | የጨረታ መነሻ ዋጋ
|
የጨረታዉ ቀን፣ ሰዓት እና ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ
|
ጨረታው የወጣው | ||
| ከተማ፣ ክ/ከ/ ወረዳ/
ቀበሌ |
የባለቤትነት መረጋገጫ ቁጥር | የቦታ ስፋት በካ.ሜ/ሄክ | ||||||||
| 1 | ሳንተን ጀነራል ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር | እነ አብረሃም አሰፋ ተሰማ | የመኖሪያ ቤት | ለም ሆቴል | በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው ከጋዜቦ አደባባይ ወደ ለገሀር የሚወስድ መሸዋለኪያ መንገድ ላይ፣ | AA000040901221 | 513 ካ.ሜ | 18,048,800.48 | ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከ3፡00-4፡00 ሰዓት በዋና መስሪያ ቤት | ለመጀመሪያ ጊዜ |
| 2 | ሳንተን ጀነራል ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር | አቶ ተክሉ አስገዶም ወ/ዮሃንስ | የመኖሪያ ቤት | ለም ሆቴል | በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ከፊጋ መብራት ወደ ጉርድሾላ የሚወስድ መንገድ ላይ፤ | AA000060703203 | 383 ካ.ሜ | 10,028,130.37
|
ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከ 4፡15-5፡15 ሰዓት በዋና መስሪያ ቤት | ለመጀመሪያ ጊዜ |
| 3 | ሳንተን ጀነራል ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር | ተበዳሪው | የሰሊጥ እና ቅመማቅመም መስኖ እርሻ መሬት ከነ መጋዘን፤ | ለም ሆቴል | በደቡብ ኢትዮጽያ ክልል ባስኬቶ ልዩ ወረዳ ቡነ ቡሳ ቀበሌ | 11284/ካአበ-226/10 | 400 ሄ/ር | 18,527,790 | ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከ3፡00-4፡00 ሰዓት በዋና መስሪያ ቤት | ለመጀመሪያ ጊዜ |
| 4. | ሳንተን ጀነራል ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር | ተበዳሪው | የአትክልት፣የፍራፍሬ፣የቅባት እህሎች እና ጥራጥሬ እርሻ መሬት መስኖ ልማት | ለም ሆቴል | በደቡብ ኢትዮጽያ ክልል ባስኬቶ ልዩ ወረዳ ቡነ ቡሳ ቀበሌ | 356/ኢ-226/01 | 508 ሄ/ር | 13,522,600 | ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከ 4፡00-5፡00 ሰዓት በዋና መስሪያ ቤት | ለመጀመሪያ ጊዜ |
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ/ሲ.ፒ.ኦ በኦሮሚያ ባንክ ስም አሰርተው ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል፡፡
- ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ቦሌ መንገድ ኦሎምፒያ አካባቢ አምራን ሆቴል ጎን የኦሮሚያ ባንክ ህግ አገልግሎት ቢሮ የሚገኝበት ናትሩት ሀውስ (ህንፃ) 9ኛ ፎቅ ላይ የሚገኝ የጨረታ አዳራሽ ውስጥ፣ባለዕዳዎቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይካሄዳል፡፡ ባለ ዕዳዎቹ ባይገኙም ጨረታው ይካሄዳል፡፡
- የተጨራቾች ምዝገባ ከሐራጅ መዝግያ ስዓት 5 ደቅቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡ የጨረታ መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ ከፍተኛ ዋጋ የሰጠ ተጫራች ካልተለየ አስኪለይ ደረስ ጨረታው የሚቀጥል ይሆናል፡፡ በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ከባንኩ ህግ አገልግሎት ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች አሸናፊ መሆኑ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ ለባንኩ አጠቃሎ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ የማያደርግ የጨረታ አሸናፊ ያስያዘው ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚፈጠረው ልዩነት ይጠየቃል፡፡
- በባንኩ ብድር ፖሊሲ መሰረት የሚፈለገውን ማስረጃ አሟልቶ ለቀረበ የጨረታ አሸናፊ ባንኩ ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ንብረቱን በማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች ግብር፣ የሊዝ ክፍያ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የስም ማዘወሪያ እና ማናቸዉም ከጨረታው ጋር በተገናኘ መንግስት የሚጠይቀው ክፍያ ይከፍላል፡፡ ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
- ውዝፍ የሊዝ ክፍያን በተመለከተ ከእዳ ተመላሽ ብር ካለ ከተመላሽ ብር ላይ የሚከፈል ሲሆን ተመላሽ ብር ከሌለ ግን የንብረቱ ጨረታ አሸናፊ ውዝፍ የሊዝ ክፍያን ሙሉ በሙሉ የሚከፍል ይሆናል፡፡
- ተጨራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች በስራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ ለመጎብኘት ይችላሉ፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 557 1372 ዋና መ/ቤት ሕግ አገልግሎት ወይም ለተራ ቁ-1 እስከ 4 በ011-6-59-14-21/08-82 ኦሮሚያ ባንክ ለም ሆቴል ቅርንጫፍ ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ባንኩ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
