Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Trading Businesses Corporation (የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን)
  • Address ደብረዘይት መንገድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114 43 12 76
  • Websitehttps://www.etbc.com.et/index.php/home
  • Deadline22 May 2026, 10:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1000.00
  • opening date2026-05-22 10:30:00
  • Categories Steel, Metals And Aluminium , Metals And Metal Working , Vehicle Spare Parts

የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን ኮርፖሬሽናችን ሳሪስ በሚገኘው ግቢ ውስጥ ያሉትን ያለገሉ ብረታ ብረቶች፣ ንቃይ ቆርቆሮች እና ቁርጥራጭ የተሽከርካሪና ሌሎች ብረታ ብረቶች ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ላላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

 

የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን ኮርፖሬሽናችን ሳሪስ በሚገኘው ግቢ ውስጥ ያሉትን ያለገሉ ብረታ ብረቶች፣ ንቃይ ቆርቆሮች እና ቁርጥራጭ የተሽከርካሪና ሌሎች ብረታ ብረቶች ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ላላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታ ላይ መወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች ማሟላት አለባቸው፡፡

1.     ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውንና የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 1,000 ብር /አንድ ሺህ/ በመክፈል ከግንቦት 7 ቀን 2018 .. እስከ ከግንቦት 14 ቀን 2018 .. ዘወትር ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ከዋናው /ቤት /አዲስ አበባ/ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 300-630 እንዲሁም ከሠዓት 730- 1130 እና ቅዳሜ 300 እስከ 6 30 ሠዓት መግዛት ይችላሉ፡፡

2.     ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት እስከ ከግንቦት 14 ቀን 2018 .. ከጠዋቱ 430 ሠዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው

3.     ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ንብረት 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በሲ.. ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡

4.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ሲሞሉ በግልጽ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ማሳየት አለባቸው፡፡

5.     ጨረታው ግንቦት 14 ቀን 2018 .. ከጠዋቱ 430 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 430 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው /ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

6.     የጨረታው አሸናፊ ተጫራች በጨረታው ያሸነፉትን ንብረት ሙሉ ክፍያ 5 /አምስት/ የሥራ ቀናት ውስጥ በመፈል ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካላነሳ 5ኛው ቀን በኋላ ላላነሳበት ቀን በየቀኑ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ቅጣት የሚከፍል ይሆናል፡፡

7.     አሸናፊው በራሱ ወጪ የተለያዩ ብረታ ብረቶች፣ ንቃይ ቆርቆሮች እና ቁርጥራጭ የተሽከርካሪና ሌሎች ብረታ ብረቶች ማንሳት፣ ማስጫንና ማጓጓዝ ይኖርበታል፡፡

8.     ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-4-16-73-47/ 011-4 66-93-36 መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

አድራሻ፡- በቅሎ ቤት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት

ስልክ ቁጥር፡- 0114 -67-19-02/011 4-16-34-83 አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ

 

የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን

Save Tender