Tender Detail

Tender Details


ኮርፖሬሽኑ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ለማንቀሳቀስ የምርት መያዣ ፕላስቲክ ሳጥን ግዥ የመንግስትን ማዥ መስፈርቶች የሚያሟሉ እና በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዥው መለያ ቁጥር: - ... ማዕከል ግዥ/ ብግጨ 06/2018 

 

ኮርፖሬሽኑ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ለማንቀሳቀስ የምርት መያዣ ፕላስቲክ ሳጥን ግዥ የመንግስትን ማዥ መስፈርቶች የሚያሟሉ እና በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። የምርት መያዣ የፕላስቲክ ሳጥን ብዛት 10,000.00 (አስር ሺህ)

1.       ተጫራቾች በዘርፋ 2018 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢ /ቤት የተሰጠ ወቅታዊ የድጋፍ ደብዳቤ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ ምዝገባ ስርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። እነዚህ ሰነዶች በቴክኒካል ፕሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ታሽገው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

2.       ተጫራቾች ከላይ የተገለጹትን ሰነዶች ከጨረታ ሰነድ ማቅረቢያው ቀነ ገደብ በፊት ማቅረብ አለባቸው። ከጨረታ መክፈቻው ቀን በኋላ የተገኘ ማስረጃ ተቀባይነት የለውም።

3.       ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (ብር አምስት መቶበመክፈል ከግንቦት 10 ቀን 2018 . ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠቱ 230 – 630 እንዲሁም ከሰአት 730 – 1100 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 230 – 630 ድረስ ማመልከቻ በመያዝ ብሎክ 2 አንደኛ ፎቅ ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ። (አድራሻው ከስር ተገልጿል.)

4.       ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት እስከ ግንቦት 19 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 430 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

5.       ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብርበሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው. ኢንሹራንስ ቦንድና ቼክ ተቀባይነት የላቸውም። የጨረታ ማስከበሪያው በቴክኒካል ፐሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ወይም ለብቻው ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል።

6.       ተጫራቾች ቴክኒክ እና ፋይናንስ ሰነድ በግልጽ ከፍለው በተለያየ ኤንቨሎፕ ለየብቻ አሽገው ማቅረብ FOID ይኖርባቸዋል።

7.       ጨረታው ግንቦት 19 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 430 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 430 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

8.       ከዋና የመወዳደሪያ ሀሳብ (ኦሪጅናል) በተጨማሪ የሚፈለጉ ኮፒዎች ብዛት 1(አንድ)

9.       አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ መጠን ለአሸነፉበት የምርት መያዣ ፕላስቲክ ሳጥን ጠቅላላ ዋጋ 10  ፐርሰንት በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ውሉን የሚፈፅሙ ይሆናል።

10.   ተጫራቾች የምርት መያዣ ፕላስቲክ ሳጥን ናሙና መቅረብ አለበት።

11.   ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን በከፊልም ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን

የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

ደብረዘይት መንገድ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርጫፍ ፊት ለፊት

... 7858

ስልክ ቁጥር 011 416 7345/ 011 466 9336

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

 

 የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን

Save Tender