የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ በስሩ የሚያስተዳድራቸው እርሻዎች በተለያዩ የምርት ዘመን ያመረተውን ምርት ብጣሪዎች (የተለያየ ደረጃ ያላቸውን) እና ያገለገለ ፒፒ ባግ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር ም-04/2018
የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ በስሩ የሚያስተዳድራቸው እርሻዎች በተለያዩ የምርት ዘመን ያመረተውን ምርት ብጣሪዎች (የተለያየ ደረጃ ያላቸውን) እና ያገለገለ ፒፒ ባግ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከድርጅቱ ጽ/ቤት አሰላ፣ ባሌ ሮቤ፣ ነቀምቴ እና አዲስ አበባ ጎተራ ተሻለ ጋራዥ ባለኬር ህንጻ ቢሮ ቁጥር 403 የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመግዛት በጨረታ መሳተፍ ይችላሉ። ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ይውላል። በ16ኛ የሥራ ቀን ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት ከቀኑ በ8፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መ/ቤት አሰላ፣ ባሌ ሮቤ፣ነቀምቴ እና በዋናው መ/ቤት አዲስ አበባ ይከፈታል።
ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 467 3862 አዲስ አበባ ወይም 022 331 3900/29 47 አሰላ ወይም 022 244 0011/85 ባሌ ሮቤ ወይም 057 660 3797 ነቀምቴ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ
