Tender Detail

Tender Details

  • Company የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር
  • Address መገናኛ ቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፊት ለፊት ወይም መገናኛ ሕዳሴ ህንጻ ወረድ ብሎ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 157 0333
  • Websitehttps://www.poessa.gov.et/
  • Deadline09 Jun 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2026-06-09 10:15:00
  • Categories Industrial Machinery Provision And Installation , Land , House, Building And Warehouse

የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ከሰራተኛው መደበኛ የወር ደመወዝ ላይ ተገቢውን የጡረታ መዋጮ ቀንሰው እና የድርጅቱን ድርሻ መዋጮ ጨምረው ለግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ ፈንድ ገቢ ባለማድረጋቸው ምክንያት በተሠጠው ሥልጣን መሰረት የድርጅቶቹን ሀብት በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

 

ስማቸው ከዚህ በታች የተመለከቱት ድርጅቶች በግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 1268/2014 አንቀጽ 12 መሰረት ከሠራተኛው መደበኛ የወር ደመወዝ ላይ ተገቢውን የጡረታ መዋጮ ቀንሰው እና የድርጅቱን ድርሻ መዋጮ ጨምረው ለግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ ፈንድ ገቢ ባለማድረጋቸው አስተዳደሩ በአዋጅ ቁጥር 1268/2014 አንቀጽ 12 ንዑስ አንቀጽ 13 በተሠጠው ሥልጣን እና አዋጁን ለማስፈጸም በወጣው መመሪያ ቁጥር 1086/2017 መሠረት የድርጅቶቹን ሀብት በግልጽ ጨረታ በመሸጥ ውዝፍ ጡረታ መዋጮ ዕዳው እንዲሰበሰብ ወስኗል።

በዚሁ መሠረት፡-

ተራ

ቁጥር

ውዝፍ የጡረታ መዋጮ ዕዳው

የሚፈለግበት ድርጅት ሥም

በቀጣይ የሚታሰብ ወለድ እና ቅጣት ሳይጨምር ከድርጅቱ የሚፈለገው የጡረታ መዋጮ ዕዳ

መጠን በብር

የካርታ ቁጥር /የሊዝ

ይዞታ ምስክር ወረቀት

ቁጥር

 

የቦታ ስፋት በካሬ ሜትር

የድርጅቱ ሀብት የሚገኝበት አድራሻ

የጨረታ መነሻ ዋጋ

1

ኤም..ቢጂ ትሬዲንግ /የተ/የግ/

15,950,806.59

751/2011

7,517.95

ሚዛን ተፈሪ ከተማ ሰፈር -5 ብሎክ 3

68,961,970.72

2

አኳድሬ የተጣራ ውሃ ፋብሪካ ወይም ሼክ  ሀቢብ ትሬዲንግ /የተ/የግ/)

7,744,514.28

መል//0008

500 / በላይ

ድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 09

51,225,932.57

3

አዲስ አበባ ቆዳ /ማህበር

9,598,398.25

ሊዝ//215/19989/01

2003

አዲስ አበባ አዲስ ከተማ / ከተማ ወረዳ 14

69,899,284.00

 

1.     ስለሀብቱ አሻሻጥ ከአስተዳደሩ የግዥ ዳይሬክቶሬት ወይም ከሕግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት መረጃ ማግኘት ይቻላል።

2.     ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ብር 200.00 በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

3.     ተጫራቾች ንብረቱን የሚገዙበትን ዋጋ በግልጽ በማስፈር በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ አድርገው አድራሻው ለግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ዋና /ቤት በማለት አስፍረው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የሥራ ቀናት ጠዋት 200 እስከ 600 ሠዓት እንዲሁም ከሰዓት 700 እስከ 1100 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በግዢ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው የግልጽ ጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።

4.     ተጫራቾች በቅድሚያ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/10ኛውን በጥሬ ገንዘብ ወይም .. ማስያዝ አለባቸው።

5.     ጨረታው 16ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 400 ሠዓት ተዘግቶ 415 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስተዳደሩ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል። የመክፈቻው ቀን የእረፍት ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት የሚከፈት ይሆናል።

6.     ተጫራቾች ይዞታውን በግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ዋና /ቤት በሚያመቻቸው ፕሮግራም በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ።

7.     አሸናፊው ያስያዘው ገንዘብ ከግዥው ዋጋ ጋር ታስቦ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ በመፈል ሀብቱና መረከብ አለበት።

8.     የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ የማይከፍል ከሆነ ለጨረታው በዋስትና ያስያዘው ገንዘብ ለአስተዳደሩ ገቢ ሆኖ የጨረታው አሸናፊነቱ ይሠረዛል።

9.     ከሽያጩ ጋር በተያያዘ የሚከፈሉ ግብርና ታክሶች፣ የስም ማዛወሪያ እንዲሁም ሌሎች ማናቸውም ሕጋዊ ወጪዎች በገዢ ይሸፈናሉ።

10. አስተዳደሩ ስለሀብቱ አሻሻጥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- መገናኛ ቦሌ /ከተማ አስተዳደር ፊት ለፊት

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011 157 0333/ 011 157 4906

 

የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር

Save Tender