የጋም/ህ/ብ/ክ/መንግሥት የአኙዋሃ ብሔረሰብ ዞን ትምህርት መምሪያ በአቦቦ ወረዳ አባሩ ቀበሌ የአዳሪ ትምህርት ቤት ለማስገንባት ስለሚፈልግ በስራ ተቋራጭነት ተመዝግቦ የሚገኝ ከደረጃ 1 BC/GC ያሉ ስራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጋም/ህ/ብ/ክ/መንግሥት የአኙዋሃ ብሔረሰብ ዞን ትምህርት መምሪያ በአቦቦ ወረዳ አባሩ ቀበሌ የአዳሪ ትምህርት ቤት ለማስገንባት ስለሚፈልግ በስራ ተቋራጭነት ተመዝግቦ የሚገኝ ከደረጃ 1 BC/GC ያሉ ስራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፣
2. የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት፣
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣
4. የታደሰ ከግብር ውዝፍ ነፃ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፣
5. ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ተጫራቾች ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 4,000.00 /አራት ሺህ/ ብር በመክፈል ከዞኑ ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ ከፍል በመቅረብ መግዛት ትችላላችሁ።
6. ተጫራቾች የጨረታውን ዋስትና ማስከበሪያ 2,000,000.00 (ሁለት ሚሊዮን) ብር በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ ብቻ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች ግንባታውን የሚያከናውኑበትን ዋጋ ዋናውንና ኮፒ ሁለት /2/ እና ካምፓኒ ፕሮፋይል ዋናውንና ኮፒ ሁለት /2/ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ በ22ተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 – 3፡30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ አስገብተው በዚሁ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በዞኑ ፋይናንስ መምሪያ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ ክፍል ይከፈታል፡፡
8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
9. ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር +251-917-77-94-35/+251-924-41-39-66 ይጠቀሙ።
በጋም/ህ/ብ/ክ/መንግሥት የአኙዋሃ ብሔረሰብ ዞን ትምህርት መምሪያ
