Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት
  • Address ሜክሲኮ አደባባይ ወይ ሣርቤት በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ዝቅ ብሎ, Phone: 011-551-3288
  • Website
  • Deadline18 Sep 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) የማይመለስ
  • opening dateSep 18, 2026, 10:05 AM
  • Categories Building Construction , Construction Works , Contractors

የሲቪል የግንባታ ሥራዎች


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡06/2019

 

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በአዋሽ ኦፕሬሽናል ነዳጅ ዴፖ ውስጥ የተለያዩ የሲቪል የግንባታ ሥራዎች በመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ለመንግስት ልማት ድርጅቶች በተዘጋጀው ለኮንስትራክሽን ስራዎች የሚውል የጨረታ ሰነድ መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት የሚችሉ ደረጃ 5 እና ደረጃ 6 የሆነ ሥራ ተቋራጮች ብቻ መወዳደር ይችላሉ።

1.      ተጫራቾች የሚከተሉትን ሠነዶች ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት (VAT)፣የግብር ከፋይነት ሠርተፍኬት (TIN)፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና ስለ ግብር አከፋፈል የተሰጠ ማስረጃ

2.    በተ.ቁ 1 ከተጠቀሱት በተጨማሪ ተጫራቾች ደረጃቸውን የሚገልጽ የታደሰ የምስክር ወረቀት፣ ለሥራው የሚያስፈልጉ መሣሪያዎችና ተሽከርካሪዎች ዝርዝር መግለጫ ለሥራው የሚያስፈልጉ የባለሙያዎች መግለጫና ዝርዝር እና በጨረታው ለተጠየቀው ሥራ ወይም ተመሳሳይ የሥራ ልምድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3.    ተጫራቾች በCPO ወይም በባንክ ጋራንቲ ብር 400,000.00 የጨረታ ማስከበሪ ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4.    ተጫራቾች ለግንባታ ስራው አንድ ኦሪጂናልና አንድ ኮፒ የመወዳደሪያ ሰነድ በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ 8/1/2019 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 602 ለዚህ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5.    ጨረታው በዚሁ ቀን 8/1/2019 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4፡05 ሰዓት ተጫራች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 602 ይከፈታል።

6.    ተጫራች የሥራውን ዓይነትና ሁኔታ በአካል በመገኘት ማየትና ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ

7.    ተጫራች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ከድርጅቱ ግዥና ትራንስፖርት ክፍል ቢሮ ቁጥር 011 መውሰድ ይችላሉ።

8.    ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:

አድራሻ፡- ሜክሲኮ አደባባይ ወይ ሣርቤት በሚወስደው 

መንገድ 300 ሜትር ዝቅ ብሎ

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ስልክ ቁጥር 011-551-3288

 

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Petroleum Supply Enterprise seeks contractors for civil construction works at Awash operational fuel depot. Open tender for Grade 5 and 6 contractors only. Bidders must provide valid trade license, VAT, TIN, supplier registration, tax clearance, renewed grade certificate, equipment/vehicle lists, expert details, and relevant work experience.
Save Tender