Tender Detail

Tender Details


 ኦሮሚያ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለሰጠው ብድር በዋሰትና የያዘዉን በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ 


የሐራጅ ማስታወቂያ

 ኦሮሚያ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለሰጠው ብድር በዋሰትና የያዘዉን በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

  ተ.ቁ የተበዳሪው ስም

 

 

የንብረት አስያዥ ስም ለጨረታ የቀረበው ንብረት ዓይነት አበዳሪው ቅርንጫፍ ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻና የቦታ ስፋት የጨረታ መነሻ ዋጋ

 

የጨረታዉ ቀን፣ ሰዓት እና ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ

 

ጨረታው የወጣው
  ከተማ፣ ክ/ከ/ ወረዳ/

ቀበሌ

የባለቤትነት መረጋገጫ ቁጥር የቦታ ስፋት በካ.ሜ/ሄክ
1 አቢሲኒያ የቄራ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ወ/ሪት ሰሎሜ አሰፋ ፈለቀ የመኖሪያ ቤት (G+2) ኦዳ አዲስ አበባ ከተማ፣ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 10፣ ፍየል ቤት አካባቢ LMK1021356379465820 94.64 ካ.ሜ 16,150,014.44 ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከ 3፡00-4፡00 ሰዓት በዋና መ/ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ
2 አቢሲኒያ የቄራ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማህበር አቶ ቴዎድሮስ ታደሰ ወላንሳ የመኖሪያ ቤት (G+2) ኦዳ አዲስ አበባ ከተማ፣ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 10፣ ፍየል ቤት አካባቢ LMK10712470994644844 94.64 ካ.ሜ 16,150,014.44 ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከ 4፡30-5፡30 ሰዓት በዋና መ/ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ
3 አቢሲኒያ የቄራ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሼባተራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለድርጅት አገልግሎት የሚውል ኦዳ አዳማ ከተማ፣ በቀድሞ አጠራር ቀበሌ 03 605/88 2,931 ካ.ሜ 38,230,080.27 ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከ 4፡00-5፡00 ሰዓት በ አዳማ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ
  የተበዳሪው ስም

 

የንብረት አስያዥ ስም የተሸከርካሪው አይነት የሚገኝበት አድራሻ የሰሌዳ ቁጥር፣ የሞተር ቁጥር እና የሻንሺ ቁጥር የጨረታ መነሻ ዋጋ    የጨረታዉ ቀንና ሰዓት ጨረታው የወጣው
የመኪና ዓይነት የሚገኝበት ቦታ የሰሌዳ ቁጥር የተሰራበት ዘመን የሻንሲ ቁጥር የሞተርቁጥር
4 አቢሲኒያ የቄራ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ተበዳሪው ጃፓን-ቶዮታ ላንድ ክሩዘር (ትዊን ቱርቦ) ቦሌ መንገድ ጌቱ ኮሜርሻል ህንጻ አጠገብ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት የተሸከርካሪ ማቆሚያ ግቢ ውስጥ አአ-03-B34719 2021 JTMAB7BJ0N4012808

 

V35A-0048910  

23,000,000.00

ሰኔ 02 ቀን 2018 ዓ.ም ከ 4፡00-5፡00 ሰዓት በዋና መ/ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ

የሐራጅ ደምቦች

  1. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ/ሲ.ፒ.ኦ በኦሮሚያ ባንክ ስም አሰርተው ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል፡፡
  2. ተ.ቁ 1፣2 እና 4 ላይ የተጠቀሱ ንብረቶች ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ቦሌ መንገድ አምራን ሆቴል ጎን የኦሮሚያ ባንክ ህግ አገልግሎት ቢሮ የሚገኝበት ናትሩት ሀውስ (ህንፃ) 9ኛ ፎቅ ላይ የሚገኝ የጨረታ አዳራሽ ውስጥ እና ተ.ቁ 3 ላይ የተገለጸው ንብረት ጨረታው አዳማ ከተማ፣አራዳ አካበቢ በሚገኝ የኦሮሚያ ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ቢሮ የሚገኝበት ህንጻ 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኝ አዳራሽ ውስጥ ባለዕዳዎቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይካሄዳል፡፡ ባለ ዕዳዎቹ ባይገኙም ጨረታው ይካሄዳል፡፡
  3. የተጨራቾች ምዝገባ ከሐራጅ መዝግያ ስዓት 5 ደቅቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡ የጨረታ መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ ከፍተኛ ዋጋ የሰጠ ተጫራች ካልተለየ አስኪለይ ደረስ ጨረታው የሚቀጥል ይሆናል፡፡ በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ከባንኩ ህግ አገልግሎት ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል፡፡
  4. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች አሸናፊ መሆኑ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ ለባንኩ አጠቃሎ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ የማያደርግ የጨረታ አሸናፊ ያስያዘው ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚፈጠረው ልዩነት ይጠየቃል፡፡
  5. በባንኩ ብድር ፖሊሲ መሰረት የሚፈለገውን ማስረጃ አሟልቶ ለቀረበ የጨረታ አሸናፊ ባንኩ ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡
  6. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ንብረቱን በማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች ግብር፣ የሊዝ ክፍያ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የስም ማዘወሪያ እና ማናቸዉም ከጨረታው ጋር በተገናኘ መንግስት የሚጠይቀው ክፍያ ማናቸውም ይከፍላል፡፡ ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
  7. በተ.ቁ 4 ላይ የተጠቀሰው ተሽከርካሪ ከቀረጥና ታክስ ነጻ ወደ ሀገር ውስጥ የገባ ሲሆን እስከ ግንቦት 04 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚፈለግበት ቀረጥና ታክስ ብር 11,325,483.70 መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  8. ውዝፍ የሊዝ ክፍያን በተመለከተ ከእዳ ተመላሽ ብር ካለ ከተመላሽ ብር ላይ የሚከፈል ሲሆን ተመላሽ ብር ከሌለ ግን የንብረቱ ጨረታ አሸናፊ ውዝፍ የሊዝ ክፍያን ሙሉ በሙሉ የሚከፍል ይሆናል፡፡
  9. ተጨራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች በስራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ ለመጎብኘት ይችላሉ፡፡
  10. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 557 13 72 ወይም 0984380868 ዋና መ/ቤት ሕግ አገልግሎት፣ወይም በ 0115-15-52-33 ኦሮሚያ ባንክ ኦዳ ቅርንጫፍ ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
  11. ባንኩ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ኦሮሚያ ባንክ  አ.ማ

 

Save Tender