Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (EBC)
  • Address ቸርችል ጎዳና፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ, Phone: 0115172521
  • Websitehttps://www.ebc.et/about.aspx
  • Deadline06 Jun 2026, 11:30 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2026-06-06 11:45:00
  • Categories Plastic Raw Materials And Products

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች የቀረበውን ግዥ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ NCB 005/2018 አወዳድሮ የአርቴፊሻል ሳር ምንጣፍና ፖስቲሽ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


ሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

NCB 005/2018

 

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች የቀረበውን ግዥ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ NCB 005/2018 አወዳድሮ የአርቴፊሻል ሳር ምንጣፍና ፖስቲሽ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ።

1.       ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊና የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ በመንግስት ግዥ ላይ ለመሳተፍ የተመዘገቡበት የአቅራቢነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት ቲን ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የግብር ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2.       ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብርብቻ በመክፈል ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በተቀመጠው ቀንና ሰዓት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ሸጎሌ ጊቢ ግዥ ዲፓርትመንት ቢሮ መግዛት ይችላሉ።

3.       ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ቢድ ቦንድ ብር 30,000.00(ሰላሳ ብርበባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ስም ሞልተው ከኦሪጅናል ቴክኒካል ፕሮፖዛል ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4.       ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ቴክኒካልና ኦሪጅናልና ሁለት ኮፒ፤ ፋይናንሽያል ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ በኢንቨሎፕ በማድረግ መቅረብ አለበት:: የኮፒ ሰነዶች ከኦሪጅናል ሰነዱ ጋር በአይነትም ሆነ በብዛት ተመሳሳይ መሆን አለበት። የጨረታውን ስምና ቁጥር በመግለጽ በኮርፖሬሽኑ ግዥ ዲፓርትመንት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5.       ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 530 ተዘግቶ ከጠዋቱ 545 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ ዋናው /ቤት ሽጎሌ ጊቢ ግዥ ዲፓርትመንት ቢሮ ይከፈታል። ሆኖም ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግስት የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ተዘግቶ ይከፈታል።

6.       ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 011-517-2521/11 ደውለው ወይም በአካል መጠየቅ ይችላሉ።

7.       ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሸን

Save Tender