Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address ሰሜን ሸዋ ዞን : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0111170171
  • Website
  • Deadline12 Jun 2026, 9:30 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price300.00
  • opening date2026-06-12 09:30:00
  • Categories Advertising And Promotion , Printed Advertising Materials

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ፦1ኛ የህትመት 8000 ብር 2ኛ/ የሬማ ከተማ የውሃ ዕቃ 10,000 ብር በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ፦1ኛ የህትመት 8000 ብር 2ኛ/ የሬማ ከተማ የውሃ ዕቃ 10,000 ብር በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

1.     በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን እንዲሁም በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ድምር ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2.     ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የጨረታ ሰነድ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

3.     ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረዉ የነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ሞልተው ኮፒና ኦርጅናል ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4.     ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የጠቅላላ ዋጋ በዝርዝር ተሞልቶ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ በተዘረዘረው ሎት የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸዉ የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሲ.ፒ.ኦ/C.P.O/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

5.     ተጫራቹ በዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ስም ፊርማና ማህተም በማድረግ በታሸገ ፖስታ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛ ቀን 3፡30 ድረስ በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6.     የጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ዕቃውን በሚ/ወ/ወ/ሴክተር መ/ቤቶች ባሉት ንብረት ክፍል ውስጥ ማድረስ ይኖርባቸዋል።

7.     የጨረታ ውድድሩ እንደ አስፈላጊነቱ በነጠላ ዋጋ ወይም በሎት ሊሆን ይችላል።

8.     ጨረታው ተጫራቾች በአካል ሆነ ህጋዊ ወኪሎቻዉ በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 18 ይከፈታል። የመከፈቻ ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ላይ የጨረታ ሰነድ የመጨረሻ ማስገቢያ ከጠዋቱ 3፡30 ሆኖ ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ጨረታው ይከፈታል።

9.     መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስ/ቁ 0111170171 ወይም 09 13 57 44 40 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

በሰሜን ሸዋ ዞን የሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

Save Tender