Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት
  • Address ሆሳዕና ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፡ ኢትዮጵያ , Phone: 046 178 4632
  • Website
  • Deadline08 Jun 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2026-06-08 14:00:00
  • Categories Vehicle (Garage Service)

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ስር ያሉ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን የጥገና አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ስር ያሉ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን የጥገና አገልግሎት በቅርበት ለመስጠት የጋራዥ ግልጽ ጨረታ አውጥቷል።

ስለሆነም በዘርፉ ልምድ ያላቸው እና ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾች በሚከተሉት መስፈርቶች መሰረት እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል።

1. የጨረታው አይነት

የተለያዩ የተሽከርካሪዎች ጥገና ፡

  • ቪ-8፣ ላንድ ክሩዘር ፣ ሀርድ ቶፕ፣ ኮብራ ስቴሽን ዋገን፣ ፕራዶ፣ኒሳን አልሜራ፣ሂኖ የጭነት መኪና ሃይ ሩፍ ሚኒ ባስ፣ ሚስቲ ቡሽ ፣ማህንድራ፣ ቢሾፍቱ እና ሌሎች ተሽከርካሪዎች

2. የተጫራቾቾ መስፈርት፡-

  • በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው
  • የTIN ቁጥር እና የVAT ተመዝጋቢ የሆነ
  • ደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ የጥገና ፈቃድ ሰርተፊኬት ያለው
  • በተሽከርካሪ ጥገና ስራ በቂ ልምድ ያለው
  • የስራ ማስረጃ እና የቀድሞ ደንበኞች ማስረጃ ማቅረብ የሚችል

3, የጨረታ ሰነድ መግዣ፡-

የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር ተከታታይ የስራ ቀናት አምስት መቶ ብር በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስተዳደር ዳይሬክቶሬት መግዛት ይቻላል።

4. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ፡-

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በአንድ በማሸግ ዘወትር በስራ ሰአት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚችሉ ሲሆን፤ ለጨረታው ማስከበሪያ አንድ መቶ ሺህ ብር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲፒኦ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።

5. የጨረታ መክፈቻ፡-

ጨረታው ከቀኑ ስድስት ሰአት ታሽጎ በዛው እለት ከቀኑ ስምንት ሰአት የሚከፈት ሲሆን ቀኑ በአል፣ ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋ/ን/አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በስምንት ሰአት ይከፈታል።

6. ማሳሰቢያ

  • ድርጅቱ የተሻለ ጥቅም ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
  • የጨረታ ሰነዶች ዘግይተው ከቀረቡ ተቀባይነት አይኖራቸውም።

 

አድራሻ: ሆሳዕና
ስልክ ቁጥር: 046 178 4632
ድርጅት: የማ/ኢ/ርዕ/መስተዳድር ጽ/ቤት


የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት

Save Tender