Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Press Agency (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)
  • Address አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-56-98-69
  • Websitehttps://press.et/
  • Deadline19 Jun 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • opening date2026-06-19 10:30:00
  • Categories Audio Visual, Photography And Filming Service And Equipment

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት የዲጂታል ሚዲያ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በድጋሚ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር፡- ፕድ 022/2018

 

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት 2018 በጀት ዓመት የዲጂታል ሚዲያ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም፤ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በወድድሩ መሳተፍ ይችላሉ።

1.     በሥራ ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ታክስ ክሊራንስና በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።

2.     ዕጩ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻል መሆኑና ግዥውን አስመልክቶ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ ግዥ ቡድን በአካል በመምጣት ይህ የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ 16 ተከታታይ ቀናት በመውሰድ የሚወዳደሩበትን ዝርዝር ዋጋ ከቫት ጋር በመሙላት የጨረታ ሰነዱን 4 በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናሉንና ኮፒዎቻቸዉን ለየብቻ በማቅረብ ጉዳዩን አስመልክቶ በተዘጋጀው በፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት ግዥ ቡድን በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

3.     ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበርያ የሚዉል ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/በድቦንድ ማስያዝ አለባቸው።

4.     በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከአደራጃቸዉ አካል የሚቀርብ የዋስትና ደብዳቤ ተቀባይነት ይኖረዋል።

5.     ጨረታው ዕጩ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው የሥራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በአቅርቦት መምሪያ ከረፋዱ 400 ሠዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 430 ሰዓት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት 1 ፎቅ በአቅርቦት መመርያ ይከፈታል፡ ሆኖም ግን የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

6.     /ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ስልክ ቁጥር 011 156 9869

ኢሜይል procurement@press.et

አድራሻ ፡ አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት

 

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

Save Tender