Tender Detail

Tender Details

  • Company Felege Hiwot Comprehensive Specialized Hospital (የፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል)
  • Address ባህርዳር ከተማ ቀበሌ 13፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0583205738
  • Websitehttps://felegehiwothospital.com
  • Deadline13 Jun 2026, 10:15 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2026-06-13 10:30:00
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment

በአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ጤና ጥበቃ ቢሮ የፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የፅዳት እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


የግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር -//አጠ/ስፔ/ 030/18

 

በአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ጤና ጥበቃ ቢሮ የፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የፅዳት እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም የሚከተሉት መስፈርቶችን አሟልታችሁ በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋበዛል።

1.     በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2.     የግብር ከፋይነት መለያ /TIN CARD/ሰርቴፊኬት ያላቸው፤

3.     አጠቃላይ የገንዘቡ መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር / እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ  /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

4.     ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተቁ 1-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

5.     አጠቃላይ ስለ ጨረታዉ ዝርዝር መግለጫ /እስፔስፊኬሽን/አና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዟል።

6.     ተጫራቾች በጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በመሙላት መወዳደር ይችላሉ።

7.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት በተከታታይ 16 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከሆስፒታሉ ማግኘት ይችላሉ።

8.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማንኛውንም ግብር ጨምሮ የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት ፐርሰንት/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ወይም በሆስፒታሉ የጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ዋናውን ደረሰኝ ከፖስታው ውስጥ አብረው ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአማርኛ ቋንቋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያው ቅፅ መሰረት የአንዱን ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ድምር ዋጋ በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሆስፒታሉ የግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 16 ቀናት 4:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ሳጥኑም በዚሁ ዕለት ከቀኑ 415 ይታሸጋል።

9.     ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ በዚሁ ቀን ከቀኑ 430 ሰዓት ይከፈታል። ቀኑ በዓል /ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

10.  ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11.  በጨረታው የሚሳተፋ አካላት ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ /ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 5738 / 058 222 0916 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

 

አድራሻ፡ ፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

ባህር- ዳር

 

በአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ጤና ጥበቃ ቢሮ የፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

Save Tender