የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለሥራ አገልግሎቱ የሚያስፈልጉትን ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩ የተለያዩ ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ ከብቁና ሕጋዊ ተጫራቾች በማወዳደር ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።
የጨርታ ጥሪ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ግ002/2019 በጀት ዓመት
የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለሥራ አገልግሎቱ የሚያስፈልጉትን ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩ የተለያዩ ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ ከብቁና ሕጋዊ ተጫራቾች በማወዳደር ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።
ስለሆነም በየዘርፉ የተሰማሩ በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ብቁና ሕጋዊ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ኤጀንሲው ጥሪ ያቀርባል።
|
ምድብ ቁጥር
|
አገልግሎት /የዕቃው ዓይነት
|
የጨረታ ሰነድ ዋጋ
|
የጨረታ ማስከበሪያ
|
|
ሎት 1
|
መንገድ ዳር የሚቀመጥ የደረቅ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ የሚውል ደስት ቢን ግዥ
|
400 ብር
|
380, 000.00 ብር በCPO
|
|
ሎት2
|
ለረጲ (ላንድ ፊል) ውስጥ ለውስጥ መንገድ ስራ የሚውል ገረጋንቲ ድንጋይ ግዥ |
400 ብር
|
210,000.00 ብር በCPO
|
|
ሎት3
|
ለረጲ (ላንድ ፊል) ውስጥ ለውስጥ መንገድ ስራ የሚውል ተለቅ ተለቅ ያለ (ቦልድ ድንጋይ ) ግዥ
|
400 ብር
|
210,000.00 ብር በCPO
|
|
ሎት4
|
ለደረቅ ቆሻሻ መሰብሰቢያ የሚወል በእጅ የሚገፋ ጋሪ
|
400 ብር
|
230,000.00 ብር በCPO
|
|
ሎት5
|
ደረቅ ቆሻሻ የሚበሰብስ እና የማይበሰብስ የሚለይበት የኤጀንሲው ሎነ እና ህትመት ያለበት ማዳበሪያ /ከረጢት) ግዥ
|
400 ብር
|
190,000.00 ብር በCPO
|
|
ሎት6
|
ለደረቅ ቆሻሻ መጥረጊያ የሚያገለግል አካፋ ግዥ
|
400 ብር
|
100,000.00 ብር በCPO
|
|
ሎት7
|
ለደረቅ ቆሻሻ መጥረጊያ የሚያገለግል ዛቢያ/ ጀምባ
|
400 ብር
|
180,000.00 ብር በCPO
|
|
ሎት8
|
የአደጋ መከላኪያ የተራፊክ ምልክት አንጸባራቂ ኮን
|
400 ብር
|
120,000.00 ብር በCPO
|
|
ሎት9
|
ግንዛቤ ለመፍጠር ለቅስቀሳ የሚያገለግል መንታርቦ ግዥ
|
400 ብር
|
30,000.00 ብር በCPO
|
|
ሎት10
|
ለመንገድ ጽዳት ስራ የሚውል መጥረግያ ግዥ
|
400 ብር
|
80,000.00 ብር በCPO
|
|
ሎት11
|
ሁነት ዝግጅት
|
400 ብር
|
30,000.00 ብር በCPO
|
|
ሎት12
|
የኮምፖስት መስሪያ ግብአቶች
|
400 ብር
|
40,000.00 ብር በCPO
|
|
ሎት13
|
የኮምፖስት ማጣሪያ ወንፊት እና የፒቪሲ ግዥ
|
400 ብር
|
50,000.00 ብር በCPO
|
1. ተጨራቾች በጨረታው ለማሳተፍ፡- በዘመኑ የታደሰ እና አግባብነት ያለው የንግድ ሥራ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችል የዘመኑ የግብር ከሊራንስ፤ እና በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ መሠረት በሚመለከተው የመንግስት ግዥ አካል ድረ-ገጽ (www.ppa.gov.et (https://www.ppa.gov.et/) ) ላይ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
2. በሎት 1 የደረቅ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ የሚያገለግል ደስትቢን ግዥ ላይ የምትሳተፉ ተጫራቾች፣ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው ዝርዝር መግለጫ (Specification) መሠረት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና (Sample) ማቅረብ ግዴታ ነው።
3. በሎት 2 እና በሎት 3 የተጠቀሱ ግዥዎች የምትሳተፉ ተጫራቾች፣ በሕግ አግባብነት ካለው አካል የተሰጠ የማምረቻ ቦታ ኳሪ እና የባለቤትነት ፈቃድ፣ ለሰብ ቤዝ (የተቆፋሪ ማዕድን) ለማውጣትና ለገበያ ለማቅረብ የሚያስችል ሕጋዊ ሰነድ ወይም በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ የተረጋገጠ የባለቤትነት ማረጋገጫ ውክልና ማቅረብ ግዴታ ነው።
4. ከሎት 4 እስከ ሎት 13 በተጠቀሱት ግዥዎች መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፣ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የምትዋዳደሩበት ዕቃ ዕቃዎች በመስፈርቱ መሰረት ናሙና (Sample) ማቅረብ ግዴታ ነው።
5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በተገለጸው ዋጋ የማይመለስ ክፍያ በጥሬ ገንዘብ በመፈጸም፣ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ 9ኛ ፎቅ መግዛት ይችላሉ።
6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለበት።የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ያለምንም ሁኔታ የሚከፈል (unconditional) መሆን አለበት።
7. አሸናፊ ተጫራች በግዥ አፈጻጸም መመሪያ መሠረት ከጠቅላላ የውል ዋጋ 10% (አሥር በመቶ) የሚሆን የውል ማስከበሪያ ማስያዝ የሚችል።
8. ተጫራቾች ለጨረታው የሚያቀርቡትን የፋይናንሺያል ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን፣ እንዲሁም የቴክኒካል ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻቸው በፖስታ በማሸግ፣ የተጫራቹን ስምና አድራሻ በግልጽ በመጻፍ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችዋል።
9. ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አሥር) የሥራ ቀናት ከቆየ በኋላ፣ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይዘጋል። በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡ 30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የቴክኒካል ሰነዱ በመንግስት ግዥ ዳይሬከቶሬት 10ኛ ፎቅ ይከፈታል። ነገር ግን የጨረታው መከፈቻ ቀን የሕዝብ በዓል ወይም ቅዳሜ እሁድ ከሆነ፣ ሌላ ማስታወቂያ ማውጣት ሳያስፈልግ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ጨረታው ይከፈታል።
10. ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ወይም በሕግ አግባብ አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው፣ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 12 75 0002
ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ
