የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት ለተለያዩ ሎተሪዎች የቅስቀሳ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ቲሸርት፣ ኮፊያ፣ ከረጢት፣ ዣንጥላ፣ እስክርቢቶ፣ የቁልፍ መያዣ፣ ቦሎ መለጠፊያ፣ ማስታወሻ ደብተር እና ቲር ድሮ ፍላግና ቤዝ ዕቃዎችን በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግለጽ የጨረታ ማስታወቂያ ውድድር አቅራቢ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ኢሎአ/010/2018
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት ለተለያዩ ሎተሪዎች የቅስቀሳ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ቲሸርት፣ ኮፊያ፣ ከረጢት፣ ዣንጥላ፣ እስክርቢቶ፣ የቁልፍ መያዣ፣ ቦሎ መለጠፊያ፣ ማስታወሻ ደብተር እና ቲር ድሮ ፍላግና ቤዝ ዕቃዎችን በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግለጽ የጨረታ ማስታወቂያ ውድድር አቅራቢ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ሁሉ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ሳይታትሞ ከመጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ለዚህ ሥራ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ስም በተከፈተ የባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000004652782 ገቢ በማድረግ ዋናውን ማስረጃ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ስም የጨረታ ማስከበሪያ ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ በማስያዝ ዋናውን ማስረጃ ከጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶችን የቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነዶችን የያዘ አንድ ዋና እና አንድ ቅጂ ለየብቻው በፖስታ በማድረግና በጽሑፍ በመለየት የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ክሊራንስ፣ የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት፣ የማጭበርበር ድርጊት ለመፈፀም ቃል የሚገባበት ቅፅ ሞልታችሁ ማህተምና ፊርማ አድርጋችሁ የመጫረቻ ሰነዶቻችሁን አሟልታችሁ በማቅረብና የጨረታ ማስከበሪያውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ እስከ ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ አለባቸው።
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ሰኔ 10 ቀን 2018 ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡
አገልግሎቱ ስለጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታወን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-126-78-16 ደውሎ መረዳት ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት
