Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው ወደ ኮዬ ፈጬ መንገድ መንገጠያ ፊት ለፊት ያለመ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114708503
  • Website
  • Deadline16 Jun 2026, 10:00 AM
  • magazineadiss zemen
  • Bid Document Price100.00
  • opening date2026-06-16 10:00:00
  • Categories Agricultural Materials , Machinery And Vehicles , Vehicle

በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ጽ/ቤት የተያዙና የተወረሱ ተሸክርካሪዎችን፣ የግብርና መገልገያ ገጀራዎችንና ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 56/2018


በጉምሩክ ኮሚሽን . ቃሊቲ ጉምሩክ ጽ/ቤት የተያዙና የተወረሱ ተሸክርካሪዎችን፣

የግብርና መገልገያ ገጀራዎችንና ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 56/2018

በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩከ //ቤት የተተው፤ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ እንዲሁም ንብረቶችን (ብዛት ያላቸው የግብርና መገልገያ ገጀራዎች (Machete) 1 የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን ሞባይሎች፣ የሞባይል ከፍሎች፣ የኤሌክትሮንክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) በግልጽና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃና መስፈርቶች ተዘጋጅቶ ከሐሙስ ሰኔ 04/2018 . ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

በመሆኑም
1. በዕቃ ግልጽ ጨረታ በሚቀርበው የግብርና መገልገያ ገጀራዎች (Machete) ላይ መሳተፍ የሚችሉት የቡና እርሻ ያላቸው አምራቾች ሲሆን ከታች በተ. 3 ከተጠቀሱት መስፈርቶች በተጨማሪ ከሚመለከተው የፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን ወይም ከብሔራዊ ደኅንነት /ቤት ዕቃውን የመግዛት ፍቃድ ሊኖራቸው ይገባል።

2. በተሽከርካሪ ግልጽ ጨረታ ለመሣተፍ ማንኛውም ዕድሜው 18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (C.P.O) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በማስገባት በጨረታው ሊሳተፍ ይችላል።

3. በዕቃ ግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የጸና የንግድ ፍቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተጨማሪ ዕሌት ታከስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ
ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ (C.P.O) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር እያይዞ በኤንቨሉፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርበት ሲሆን ለሐራጅ ጨረታ ደግሞ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ይዞ ማስመዝገብ ይኖርበታል።

4. በጨረታው ላይ የተሸከርካሪ ወይም የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም።

5. ተጫራቶች የተሽከርካሪውንና የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ ከሐሙስ ሰኔ 04/2018 . ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (እንድ መቶ) በመክፈል በቅ//ቤቱ በመግኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።

6. በዕቃና ተሸከርካሪ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ወይም ተሸከርካሪዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በቅ//ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMISSION ADDIS ABABA KALTY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሠርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

7. የዕቃ ሐራጅ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ለዕቃዎች ብር 100,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በተ. 6 በተገለጸው አድራሻ ተጫራቹ ማስያዝ አለበት። ነገር ግን በዕቃ ሐራጅ በጨረታ ሰነድ ላይ በሚገለጹ የተወሰኑ ዕቃዎች ላይ የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) መጠን የሚወሰን መሆኑን እንገልጻለን።

8. ተጫራች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሠረት መጫረት ይችላሉ።

.

የቅ//ቤቱ  ስም

የጨረታው  አይነት

የንብረትመመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ

የጨረታው የመዝጊያና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

የዕቃ  ሐራጅ

እስከ 08/10/2018

09/10/2018 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል።

የዕቃ ግልፅ

እስከ 09/10/2018

10/10/2018 3:45 ተዘግቶ በዚያው ቀን 400 ሠዓት ይከፈታል።

የተሸከርካሪ ግልጽ

እስከ 09/10/2018

10/10/2018 3:45 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 400 ሠዓት ይከፈታል።


9. የጨረታው መከፈቻ ቦታ፡- . ቃሊቲ ጉምሩክ //ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች/ ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
10. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ 3 የሥራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
11. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ 5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል።
12. ከላይ በተ/ 11 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭይቀርባል።
13. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ ሙበቱ የተጠበቀ ነው። ለተጨማሪ
መረጃ በስልክ ቁጥር፦ አዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩከ -011 - 470-85 03
አድራሻ፡- ሳሪስ አቦ / በቀለበት መንገድ ወደ ማሠልጠኛ በሚወስደው ወደ ኮዬ ፈጬ መንገድ መንገጠያ ፊት ለፊት ያለው ሕንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ

በጉምሩክ ኮሚሽን .አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

Save Tender