ስፋቱ 233 ካሬ ሜትር የሆነ ቤት የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ
አፈ/ከሳሾች፦ እነ ኢትዮጵያ ሙሉአለም 3 ቁጥር ሰዎች
ጠበቃ፦ ባህታ ሓጎስ
አፈ/ተከሳሽ፦ አቶ ራሕመት ገ/ስላሴ
ጠበቃ ፦አብርሃ በርሀ መካከል ባለው የአፈፃፀም ክርክር ጉዳይ አስመልክቶ በመቐለ ከተማ ሰሜን ክ/ከተማ ቀበሌ ላጪ ዓዲ ጭዕንዶግ የሚገኝ አዋሳኝ
- በምሥራቅ መንገድ - በሰሜን፦ ሎታ ቁጥር 001
- በምዕራብ፦ ሎታ ቁጥር 009 -በደቡብ፦ ሎታ ቁጥር 011
ስፋቱ 233 ካሬ ሜትር የሆነ በአፈፃፀም ተከሳሽ ስም የሚታወቅ ቤትና ቦታ በመነሻ ዋጋ 5,591,352 90 (አምስት ሚሊዮን አምስት መቶ ዘጠና አንድ ሺህ ሶስት መቶ ሃምሳ ሁለት ብር ከ90 ሳንቲም) ለመጫረት ስለተፈለገ በጨረታው ለመሳተፍ የፈለገ ሰው ጨረታ የሚካሄድበት ቀን ለ02/11/2018 ዓ/ም 3:00 ሰዓት ተከፍቶ 6:30 ሰዓት የሚያልቅ ልክ 6:31 ሰዓት የሚዘጋ ሆኖ በተገለፀው ሰዓት ቀርቦ እንዲጫረት ጨረታ አሸናፊ ለጊዜው 25% እንዲያስይዝ ቀሪው 75% ደግሞ በ15 ቀን ውስጥ አሟልቶ እንዲከፍል ስም ለማዛወር አስፈላጊ ክፍያዎች ደግሞ በጨረታ አሸናፊ ራሱ የሚሸፈን መሆኑ የጨረታ ውጤት ደግሞ በዚህ ጨረታ የሚካሄድበት ቀን 02/11/2018 ዓ/ም 8:00 ሰዓት የጨረታ ውጤት የሚቀርብበት መሆኑ ተገልፆ ማስታወቂያውን በአዲስ ዘመን እንድታወጡ የመቐለ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዟል።
ማሳሰቢያ፦ በአዲስ ዘመን የሚወጣበት ቀን 30/9/2018 ዓ/ም ነው።
በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መቐለ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት
