በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በጌዴኦ ዞን የገደብ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ዩኒት ለከተማ አቀፍ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ቋሚና አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን ማለትም፡- ሎት-1- እስቴሽነሪ፣ ሎት-2-ፈርኒቸር፣ ሎት-3 ኤሌክትሮኒከስ፣ ሎት-7-የሞተር ሣይከል የመብራት ፖውዛ ዕቃዎች ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩት ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ መሰያ ቁጥር 001/2019
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በጌዴኦ ዞን የገደብ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፐላን ዩኒት ለከተማ አቀፍ ሴከተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ቋሚና አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን ማለትም፡- ሎት-1- እስቴሽነሪ፣ሎት-2-ፈርኒቸር፣ ሎት-3 ኤሌከትሮኒከስ፣ሎት-7-የሞተር ሣይከል የመብራት ፖዉዛ ዕቃዎች ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩት ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቶች :-
በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፤
የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው!
የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
ከላይ በዝርዝር የተቀመጡትን መስፈርቶችን - የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 30 የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሠነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 400 ብር/አራት መቶ ብር/በገደብ ከተማ ገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመከፈል ገንዘብ የከፈሉበትን ደረሰኝ ሲያቀርቡ የጨረታ ሰነድ ከግዥ ከፍል ማግኘት ይችላሉ።
ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዕቃ የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል፤ ቫትን ያላካተተ ከሆነ ቫትን እንደተካተተ ተደርጎ ይቆጠራል።
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ፦
ለእስቴሽነር 90.000 ሺህ ብር ፣ፈርኒቸር 75,000 ሺህ ብር ለኤሌክትሮኒክስ 235.000 ሺህ ብር፣የሞተር ሣይከል ግዥ-195,000 ሺህ ብር፣የመብራት ፖውዛ 204,000 ሺህ ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO እና ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የከፍያ ማዘዣ ቼከ ወይም በባንክዋስትና ሆኖ በጥሬ ገንዘብ ዋስትና ማቅረብ አይቻልም።
ተጫራቾች ዕቃዎች የሚሸጡበትን ዋጋ በተዘጋጀዉ ዝርዝር ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልተው አንድ ኦርጅናል ሰነድ እና ሁለት ኮፒ ሰነድ በተለያዩ ፖስት ካሸጉ በኋላ ከሲፒኦ ጋር በአንድ ትልቁ አናት ፖስታ በስም በማሸግ ማቅረብ ይኖርበታል።
ማንኛውንም ዓይነት የጨረታ ሰነድ ስርዝ፣ድልዝ ያለው ተቀባይነት የለም። አይኖርም)
በእያንዳንዱ በጨረታ ሰነድ ላይ ህጋዊ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ መኖር አለበት።
ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ በአየር ላይ ከዋለበት በተከታታይ የሥራ ቀናቶች በሚቆጠር 30 ቀናት ቦኋላ በሥራ ቀን የጨረታ ሳጥን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ላይተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ስለሆነም ተጫራቾች በዕለቱ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ከላይ የተገለጹ ቀናቶች የሥራ ቀን ካልሆኑ በሚቀጠለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታዉ የሚከፈት ይሆናል።
የጨረታ ሳጥኑ የሚገኘው በጌዴኦ ዞን በገደብ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ግዥና ንብ/አስ/ር ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ነው።
ተጫራቾች በጨረታው ተወዳድረው ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ገደብ ከተማ አስ/ር ሩይናንስ ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ የማጓጓዝ ፣የማስጫኛ እና የማውረጃ ወጪ ችለው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ ማብራሪያ - በስልክ ቁጥር 092650 4488 0926060263/0915932349መደወል ይቻላል ።
በጌዴኦ ዞን የገደብ ከተማ አስ/ር ፋይናንስና ፕላን ዩኒት
