የምሥራቅ ባሌ ዞን ማረሚያ ቤት አስተዳደር ፅ/ቤት ውስጥ ለሚገኙት የህግ ታራሚዎች በምግብ እቅርቦት የሚውል ጥሬ እህል ማጣፈጫ እና የማገዶ እንጨት ለ2019 ዓ.ም በጀት ለአንደኛ ዙር ከሀምሌ 1/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 30/04/2019 ዓ/ም ለ6 (ስድስት) ወር በሚቆይ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ለአንደኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የምሥራቅ ባሌ ዞን ማረሚያ ቤት አስተዳደር ፅ/ቤት ውስጥ ለሚገኙት የህግ ታራሚዎች በምግብ እቅርቦት የሚውል ጥሬ እህል ማጣፈጫ እና የማገዶ እንጨት ለ2019 ዓ.ም በጀት ለአንደኛ ዙር ከሀምሌ 1/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 30/04/2019 ዓ/ም ለ6 (ስድስት) ወር በሚቆይ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት ማንኛውም በጨረታ ውሉ መካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ፡-
1. የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ወይም ቢሮ የዘመኑን የስራ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና አግባብነት ያለው 2018 የታደሰ ንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል።
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TEN)የተመዘገቡ ወይም የተጨማሪ እሴት ታከስ(VAT) ከፋይመሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው ::
3. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 30(ሰላሳ ብር) በመከፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከዞኑ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ፅ/ቤት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በዞን ማረሚያ ቤት አስ/ፅ/ቤት ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር አለባቸው:
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከመቶ ሁለት (2%) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) እና የምግብ እህል ናሙና ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው።
6. በጥቃቅን እና አነስተኛ ንግድ ተደራጅቶ የበሰለ ምግብ ለማቅረብ የሚቀርቡ ማህበራት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል። ይህ ካልተገኘ በጥሬ እህል እናወዳድራለን ።
7. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን በስራ ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ያስገቡበት ሳጥን ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት በዞኑ ማረሚያ ቤት አስ/ፅ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም የህግ ታራሚ ኮሚቴዎች እና የማረሚያ ቤቱ ጨረታ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ይከፈታል።
8. የዞኑ ማረሚያ ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. በማረሚያ ቤቱ ውስጥ በተዘጋጀ ማብሰያ ቤት ውስጥ ምግብ አብስሎ ማቅረብ የሚችል ማረሚያ ቤቱ የሚገኙበት ከተማ
|
ተ.ቁ
|
የዞን ማረሚያ ቤት
|
የሚገኙበት ከተማ
|
|
1 |
የምሥራቅ ባሌ ዞን ማረሚያ ቤት
|
ጊንር
|
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0911645276 /0911803891 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
በኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን
የምሥራቅ ባሌ ዞን ማረሚያ ቤት አስተዳደር/ፅ/ቤት
