Tender Detail

Tender Details


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አቃቂ በሚገኘው የኢትዮጵያ የፋይናንስ ጥናት ተቋም ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ፣ብረት በር ፣ አልሙንየም እና የእንጨት ፓሌቶች  ፍላጎት ላላቸው ተ.እ.ታ ተመዝጋቢ ለሆኑ ድርጅቶች  በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ ብረት በር ፣ አልሙንየም እና የእንጨት ሌቶች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አቃቂ በሚገኘው የኢትዮጵያ የፋይናንስ ጥናት ተቋም ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ብረት በር አልሙንየም እና የእንጨት ፓሌቶች  ፍላጎት ላላቸው ተ.እ.ታ ተመዝጋቢ ለሆኑ ድርጅቶች  በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ፡-

  1. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ድርጅት የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በሚመጣበት ወቅት የድርጅቱን መታወቂያ ዋናውን እና ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ከሰኔ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በባንኩ ህንፃ ቁጥር 2 ምድር ቤት ላይ በሚገኘው ባንኪንግ እና ፐይመንት ሲስተምስ ዳይሬክቶሬት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ስም በሂሳብ ቁጥር 7002010800001 የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ገቢ በማድረግ እና ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ይዞ በመቅረብ በህንፃ ቁጥር 2 2ኛ ፎቅ ፋሲሊቲ ዳይሬክቶሬት በመቅረብ ለጨረታው መረጃ ማግኘትና የጨረታውን ሰነድ በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ጨረታውን ለመሳተፍ ውጤት እንደታወቀ የሚመለስ የእንጨት ፓሌቶች ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺ ብር) እና ብረታ ብረቶች ብረት በር አልሙንየም ብር50,000.00 (ብር ሃምሳ ሺ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቢድ ቦንድ (ሲ.ፒ.ኦ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከገዙበት ክፍል የበር መግቢያ ፍቃድ በመውሰድ እና የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ንብረቶቹን ባሉበት ማየት ይቻላሉ፡፡
  5. ተጫራቶች ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ብረት በር አልሙንየም እና የእንጨት ፓሌቶች የሚገዙበትን ዋጋ ማስረከቢያ ቅፅ ላይ በማካተት በስም በታሸገ ኢንቨሎፕ ሙሉ አድራሻውን እና የጨረታውን ቁጥር በመጥቀስ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በህንፃ ቁጥር 2 ሁለተኛ ፎቅ ፋሲሊቲ ዳይሬክቶሬት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  7. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ  

በስልክ ቁጥር 0115175191/0115175193/0115175223 ደውሎ መጠየቅ ይችላል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ

Save Tender