በድሬደዋ አስ/ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጽ/ቤት ቀጥሎ በሰንጠረዡ የተመለከቱትን ያገለገሉ ንብረቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ተጫራቾችን ይጋብዛል።
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በድሬደዋ አስ/ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጽ/ቤት ቀጥሎ በሰንጠረዡ የተመለከቱትን ያገለገሉ ንብረቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ተጫራቾችን ይጋብዛል።
|
ተ.ቁ |
የንብረቱ ዓይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
|
1 |
Nissan double cabin ሞዴል jd22 |
በቁጥር |
1 |
|
2 |
Nissan double cabin ሞዴል JNICJUD2270 |
በቁጥር |
1 |
|
3 |
Mitsubishi double cabin ሞዴል L-200 |
በቁጥር |
1 |
|
4 |
ልዩ ልዩ ዓይነት ያገለገሉ 9 ሞተርሳ ይክሎችና 2 የመኪና ቦዲ |
በቁጥር |
2 |
|
5 |
አገልግለው የተቀየሩ ልዩልዩ ዓይነትና መጠን ያላቸው ጎማዎች |
በቁጥር |
ከ 900 በላይ |
|
6 |
ቁርጥራጭ ብረታ ብረትና ለህክምና ያገለገሉ ብረት ነክ የላብሯቶሪ ዕቃዎችና ሌሎች ብረት ነክ ዕቃዎች |
በኪ.ግ ግምት |
ከ 500 ኪ.ግ በላይ |
|
7 |
ልዩ ልዩ ዓይነትና መጠን ያላቸው ቁርጥራጭ Aluminum profiles |
በኪ.ግ ግምት |
ከ 4000 ኪ.ግ በላይ |
|
8 |
ልዩ ልዩ ዓይነትና መጠን ያላቸው የmarble, granite እና ceramic ጡቦች |
በካፌ |
300 በላይ |
|
9 |
ልዩ ልዩ ዓይነት የኤሌክትሮኒክስና በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ዕቃዎችና ፍሪጆች አገልግሎት ሰጥተው የተቀየሩ ቀላል የተሸከርካሪ ዕቃችና ባትሪ፣ያገለገሉ የእንጨት ውጤቶችና ወንበሮች፣መጽሔትና እና ብሬይል መጽሐፍት |
|
|
ከላይ በሰንጠረዡ የተዘረዘሩት ንብረቶች ሁሉም በድሬደዋ ከተማ በሚገኘው የድሬደዋ-ደወሌ ም/ባቡር ድርጅት ግቢ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደርይችላሉ -
1. ተጫራቾች በድሬደዋ አስ/ ፋይናንስና ኢ/ል/ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገ/ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 204 በመምጣት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 18 ተከታታይ ቀናት ማለትም ከሰኔ 5 /2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 22/ 2018 ዓ.ም 11፡00 ሰዓት ድረስ የዕቃዎቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
2. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ለሽያጭ የተዘጋጁትን ንብረቶች ከሰኔ 5/2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 22/ 2018 ዓ.ም ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ከ3፡00 እስከ 1፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ድሬደዋ ከተማ በሚገኘው በድሬደዋ-ደወሌ ም/ባቡር ድርጅት ግቢ በመገኘት መመልከት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ንብረት ለጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተገለፀውን የብር መጠን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በድሬደዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጽ/ቤት ስም አሰርተው ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሣጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት በመምረጥ የሚገዙበትን ዋጋ በአኃዝና በፊደል ለይተው ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ጽፈው ከፈረሙ በኃላ በኤንቬሎፕ አሽገው በአስተዳደሩ የግዥና ንብረት ማስወገድ አገ/ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 204 በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ከሰኔ 5 /2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 23/ 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
5. ጨረታው ሰኔ 23/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ በ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ በ 4፡15 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት ማስወገድ አገ/ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 204 ውስጥ ይከፈታል፡፡
6. የጨረታ መገምገሚያ መስፈርት ከፍተኛ ዋጋ እና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ ናቸው፡፡
7. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ 7 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ከፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መከፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፣
8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመከፈል ዕቃውን በ 10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፣
9. ጽ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ ማብራሪያ :- በስልክ ቁጥር 0254 11 01 64 /0912273839 በመደወል ወይም ንብረት ማስወገድ ኬዝ ቲም ቢሮ ቁጥር 204 በመምጣት ተገቢውን መረጃ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በድሬደዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ
የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጽ/ቤት
