Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address አዋሽ ፡ አፋር ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-13-97-49-27
  • Website
  • Deadline20 Jun 2026, 9:45 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price100.00
  • opening date2026-06-20 21:45:00
  • Categories Equipment And Accessories , Equipment

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ሕግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በ 13/10/2018 ዓ/ም በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአዋሽ ጉምሩክ //ቤት የጉምሩክ ሕግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ //ቤት  13/10/2018 / በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ //ቤት በአካል በመገኘት መግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ //ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት በተጫራች ስም የማይመለስ 100 (አንድ መቶብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የዕቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየትና እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን የእቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩክ //ቤት፣ ከአዋሽ ጉምሩክ //ቤት በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆኑንና ወደ ቃሊቲ እንዲመጣልዎት የምትፈልጉት የዕቃ ናሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን በስልክ ቁጥር፡- 022-224-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ //ቤት እንዲመጣልዎት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

የጨረታ መስፈርቶች፡-

1.     ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልግ ተጫራች በጨረታ ከሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንሰ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስ ሴያቸውን ለታክስ ማዕከሉ ያሳወቁበት፣ በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል።

2.     ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 13/10/2018 . ባሉት ቀናት እስከ ጠዋቱ 345 ሰዓት እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ በዚሁ ቀን እስከ ረፋዱ 500 ሰዓት የዕቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ //ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ //ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር / በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይችላሉ።

3.     ለግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (cpo) የሚወዳደሩበት ዕቃ ኮድ 5% እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት ዕቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብርበባንክ አሠርተው በአዋሽ ጉምሩክ //ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4.     ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (እስኬጁልመሰረት በቃሊቲ ///ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ።

የጨረታ ቦታ

 

የጨረታ ዓይነት

 

ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች

 

የዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ

 

የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

 

ቃሊቲ ጉምሩክ

 

ግልጽ እና ሐራጅ

 

ጫማዎች፣ አልባሳት ኮስሞቲክስ፣ የሚኪና መለዋጫ ኤሌከትሪክ እቃዎች የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ ምግብ ነክ፣ እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች

 

ለግልጽ ጨረታ እስከ 13/10/18 ቅዳሜ ጠዋቱ 345 እና ለሃራጅ ጠዋቱ 4:45

 

ለግልፅ ጨረታ 13/10/2018 ጠዋት 345 እና ለሐራጅ ጨረታ እስከ 5:00

 

 

5.     የጨረታው መከፈቻ ቦታ በቃሊቲ ///ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።

6.     ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (C.P.O) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ የሥራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

7.     አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዘን ማውጣት ይኖርባቸዋል።

8.     ከላይ በተ..7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

9.     //ቤቱ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር- 022-224-1402 ደውለው ስለጨረታው መረጃ መጠየቅ ይቻላል።

 

የአዋሽ ጉምሩክ //ቤት

Save Tender