ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር በድርጅታችን አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ የተለያዩ ፈርኒቸሮች፣የአይቲ ዕቃዎች፣የጽዳት ማሽነሪዎች፣የማሸጊያ ፕላሰቲክ፣መጠረዣ ሪንግ ወ.ዘተ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
| ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
የጨረታ ማስታወቂያ CN/DE/02/18 |
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር በድርጅታችን አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ የተለያዩ ፈርኒቸሮች፣የአይቲ ዕቃዎች፣የጽዳት ማሽነሪዎች፣የማሸጊያ ፕላሰቲክ፣መጠረዣ ሪንግ ወ.ዘተ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 300.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሠዓት 7፡00-11፡00) ማግኘት ይቻላል፡፡ ተጫራቾች የዕቃዎቹን ሁኔታ ቀጠሮ በማስያዝ ገርጂ በሚገኘው የድርጅቱ የዕቃ ግምጃ ቤት፣ ቃሊቲ በሚገኘው ጃቲ የዕቃ ግምጃ እንዲሁም አማልጋ የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ ግምጃ ቤት በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ከጨረታ ዋጋቸው ጋር የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 በሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋርንቲ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት ጠዋት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው
የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል
ስልክ ቁጥር 011-156 99 92
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
