ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለተለያዮ ድርጅቶች ለሚሰጠው የሥራ አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውሉ የዊንች መጠለያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈፀም ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
CN/NCB/37/18
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለተለያዮ ድርጅቶች ለሚሰጠው የሥራ አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውሉ የዊንች መጠለያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈፀም ይፈልጋል።
በመሆኑም ከደረጃ (6) ስድስት በላይ የሆናችሁ የስራ ተቋራጭ ወይም ኮንትራክተር፣ የታደስ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፤ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ፣ የተጭማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ እና የሥራ ዝርዝር መግለጫ በተለየ በስም በታሸነ ፖስታ እንዲሁም የግንባታ ሥራዎች የምታከናውኑበትን ዋጋ በተለየ በስም በታሸነሁለተኛ ኤንቨሎፕ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋበዛል፡፡ የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ (ጠዋት 2፡00-6፡ 00 እንዲሁም ከሠዓት 7፡00-11፡00) ማግኘት ይቻላል። የጨረታ ማስከበሪያ ብር100,000 በባንክ በተረጋገጥ ሲፒአ ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ተጫራቶች የመቸጫረቻ ዶክመንታቸዉን ከላይ በተጠቀሰዉ አድራሻና የሰራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት ጠዋት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ከላይየተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ውጪ ይደረጋል፡፡
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ቦሴ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው
የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል
ስልክ ቁጥር 011-555 19 11
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃላ.የተ.የግ.ማኅበር
