የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ንፋስ ስልክ ላክ/ከተማ ካዲስኮ አካባቢ የሚገኘውን እና ቀደሞ ለግዥ ማማከር ንግድ ስራ ዘርፍ ለቢሮ አገልግሎት ሊሰጥ የነበረውን ባለ 2 ወለል (G+2) ህንፃ ባለበት ሁኔታ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ላላቸው ድርጅቶች በየሁለት ዓመቱ በሚታደስ ውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ የሕንፃ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ንፋስ ስልክ ላክ/ከተማ ካዲስኮ አካባቢ የሚገኘውን እና ቀደሞ ለግዥ ማማከር ንግድ ስራ ዘርፍ ለቢሮ አገልግሎት ሊሰጥ የነበረውን ባለ 2 ወለል (G+2) ህንፃ ባለበት ሁኔታ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ላላቸው ድርጅቶች በየሁለት ዓመቱ በሚታደስ ውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሎት 15 (አስር አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው!
- የተዘጋጀውንና የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር00 ሰባት ብር/ በመክፈል ከሰኔ 3 ቀን 2018 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀነ- 6፡30 እንዲሁም ከሠዓት ከቀኑ 7፡30 እስከ 11፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 6፡30 በቅሎ ቤት ከሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ዋ/መ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው መግዛት ይችላሉ፤
- ተጫራቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ህንፃው የሚገኝበት ቦታ በአካል ቀርበው መመልከት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት እስከ ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጧቱ 4፡ 30 ሠዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 / አስር ሺህ ብር/ በሰ..ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ከጨረታ ስነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ሲሞሉ በግልጽ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ NAT/ ማሳየት አለባቸው፤
- ጨረታው ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጧቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጧቱ 4፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው መ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፤
- ተጫራቾች በመወዳደሪያ ሰነዳቸው የድርጅታቸውን ስም፣ ፊርማ እና ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል፤ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው የተጫራቹን አጭር ፊርማ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የሰጡትን ዋጋ መለወጥም ሆነ ማሻሻል አይችሉም፤
- የጨረታው አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነታቸው በተገለፀ በ 10 /አሥር/ የሥራ ቀናት ውስጥ በመቅረብ ውል መዋዋል ይኖርባቸዋል፡፡ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርበው ካልተዋዋሉ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ተወርሶ ኮርፖሬሽኑ ሌላ አማራጭ የሚወስድ ይሆናል፤
- ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
- ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0114-16-34-83 መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን
አድራሻ፡- በቅሎ ቤት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር 0114-16-34-83 አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ
