ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃ አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም 8 ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ለሁስተኛ እና ስሦስተኛ ጊዜ የወጣ የጫረታ ማስታወቂያ
ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃ አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም 8 ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት፡-
ለሁለተኛ ጊዜ ጨረታ የሚወጡ የእቃ የአገልግሎት ግዥ
ሎት 1 የፕሪንተር፣ ፎቶ ኮፒ፤ ፋክስ ስካነር ጥገና እና ቀለም ሙሌት ግዥ ለሦስተኛ ጊዜ ጨረታ የሚወጡ የእቃ/ የአገልግሎት ግዥ
ሎት 2 የፓወር ኢንቨንተር Power inventor ጥገና አገልግሎት
ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች ማሟላት ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው፡፡
1. ተጫራቾች በዘርፋ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደስ የ2018 ዓ.ም ንግድ ፍቃድ ያላቸውና 1 የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ TIN እና VAT ሰርተኬት ያላቸው፣ የገቢዎች ከሊራንስና ጨረታ ለመሳተፍ ከሀገርውስጥ ገቢ የተሰጣቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴርበአቅራቢዎች ዝርዝር የምዝገባ ፈቃድ የተመዘገቡና የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. ተጫራቾች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የስራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት የታደሰ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞከራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ፌዴራል ፖሊስ የግል የተቋማት ብቃት ማረጋገጫ ምስከር ወረቀት የታደሰ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ በባንክበተረጋገጠ ሲፒኦ CPO ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
6. ለእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በድርጅታችን አዲሱ ፍልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመክፈል ከድርጅቱ ግዥ አቅርቦት ቡድን መሪ ቢሮ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊትና ከነቫቱ ተብሎ በኢትዮጵያ ብር መግለፅና መሆን አለበት፡፡ ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻውን፣ ፊርማውንና ማህተም አሟልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
8. ጨረታ ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሠነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም፡፡ ዕቃው የሚቀርብበት ጊዜ፣ ቦታና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መገለጽ አለበት፡፡ ስለዕቃው ዋስትናና የዋስትና ጊዜ በግልጽ መገለጽ አለበት፡፡
9. ጨረታ በሚመለከት ለማሸነፍ እንዲረዳዎት ለማንኛውም ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታ የሚሰረዝ ሲሆን አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ ይሰረዛል፡፡
10. ድርጅታችን የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በመጠን ወይም በዋጋ እስከ 25% በመጨመር ወይም በመቀነስ መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ መታወቅ ይኖርበታል፡፡
11. ተጫራቾች የሚመረቱትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በሰም የታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው ጠዋት በዕለቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡
12. ተጫራቾች በሚጫረቱበትን የግዥ አይነት መሠረት የተሟላ የቴከኒካል ሰነድ እና ፋይናሽያል በተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ Bid document መሰረት ጨረታ ሰነዳችሁ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ የጨረታው ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ _ ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ ለብቻው እና ፋይናሽያል ሰነድ ለብቻው በጨረታ ሣጥኑ ማስገባ አለባቸው፡፡
13. የጨረታ ሂደት የቴክኒክ ግምገማ ለሎት 1 ድርጅቱ በሚያወጣው መስፈርት መሠረት ከቴከኒከ ሠነድ ግምገማና ድርጅታዊ ብቃት ግምገማ ውጤት (60%) እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምግማ ውጤት (40%) ሲሆን እንደዚሁም ለሎት 2 ድርጅቱ በሚያወጣው ስፔስፊኬሽን/Specification/ ግምገማ (40%) እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምግማ ውጤት (60%) ድምር ውጤት አሸናፊ የሚለይ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ፡፡ ነገር ግን ቴከኒካልና ስፔስፊኬሽን/Specification/ ግምገማ ሰነድ ወይም ድርጅታዊ ብቃት ግምገማ ያላለፈ ተጫራች ድርጅት ፋይናንሺያል ሠነድ እንደማይከፈት እንዲታወቅ፡፡ የመገምገሚያ መስፈርቶቹ በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ማየት ይቻላል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስበስጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 0115 53 07 67/0115 15 73 37
የፍልዉሃ አገልግሎት ድርጅትድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስበስጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 0115 53 07 67/0115 15 73 37
የፍልዉሃ አገልግሎት ድርጅት
