Tender Detail

Tender Details

  • Company የስልጤ ዞን የወራቤ ማረሚያ ተቋም
  • Address ስልጤ ዞን ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0911804123
  • Website
  • Deadline03 Jul 2026, 7:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price150.00
  • opening date2026-07-04 09:00:00
  • Categories Food And Beverage , Food Items And Drinks , Firewood

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ማረሚያ ቤቶች አስ/ር ኮሚሽን የስልጤ ዞን የወራቤ ማረሚያ ተቋም በ2019 በጀት ዓመት በህግ ጥላ ስር ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች ለምግብ አገልግሎት የሚሆን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2019

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ማረሚያ ቤቶች አስ/ ኮሚሽን የስልጤ ዞን የወራቤ ማረሚያ ተቋም 2019 በጀት ዓመት በህግ ጥላ ስር ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች ለምግብ አገልግሎት የሚሆን፡- በሎት 1 ቅጭቅጭ የወጣለት የተበጠረ ሰርገኛ ጤፍ፣ በቆሎ፣ አተር፣ ፍርኖ ዱቄት፣ ባቄላ በሎት 2 አንበሳ ሻይ ቅጠል፣ ጨው፣ ስኳር፣ ዘይት

በሎት 3 ጎመን ዘር፣ የተፈጨ በርበሬ፣ ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ሞኮረኒ፣ ፓስታ፣ ሩዝ፣ ምስርከከ፣ አተር ከከ እና የተለያዩ ቅመማ ቅመም በሎት4 የማገዶ የባህር ዛፍ እንጨት ከሐምሌ 1/11/2018 . እስከ ታህሳስ 30/4/2019 . በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሠረት፡-

1.     በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመደቡ

2.     የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉና የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ

3.     ቫት/NAT/ ተመዝጋቢ የሆነ

4.     ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ 60 ቀናት

5.     አሸናፊው ማንኛውንም ወጪ በራሱ ሸፍኖ ዕቃዎችን ወራቤ ማረሚያ ተቋም ቅጥር ግቢ ማቅረብ የሚችል

6.     የጨረታው ማስከበሪያ 5000 (አምስት ሺህ ብር) በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ እውቅና ያለው የፋይናንስ ተቋም የተረጋገጠ ቼክ፣ ሌተር ኦፍ ክሬዲት፣ ሲፒኦ ማቅረብ የሚችሉ

7.     በጨረታው አሸናፊ የሚሆኑ ታጫራቾች በአሸነፉባቸው ዕቃ አይነቶች 10% ማስያዝ የሚችል

8.     ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ለሚወዳደሩበት አቅርቦት በዘርፉ የማይመለስ ብር 15 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) በመከፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከግዥና ፋይናንስ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ

9.     ታጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውንና የመወዳደሪያ ሂሳባቸውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ፎቶ ኮፒ እስከ 15ኛው ቀን 1100 ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው

 

10.                        ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጠበት ቀን ጀምሮ 15ኛው ቀን ከቀኑ 100 ሰዓት ታሽጎ 16ኛው ቀን 300 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 300 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

11.                        ተቋሙ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 0911804123 መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የወራቤ ማረሚያ ተቋም

 

Save Tender