የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ስርዓት ደንበኛ የሆነው ሀርቨስት ሞደርን እርሻ መካናይዜሽን አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለግብርና ሜካናይዜሽን ፕሮጀከት አገልግሎት ከባንኩ በኪራይ የወሰደውን የእርሻ ትራከተር እና ማረሻ የማሽን የኪራይ እና የአገልግሎት ከፍያ በገባው ውል መሰረት ሊፈጽም ባለመቻሉ ምከንያት ባንኩ መልሶ የተረከባቸውንና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች
የዝግ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ስርዓት ደንበኛ የሆነው ሀርቨስት ሞደርን እርሻ መካናይዜሽን አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለግብርና ሜካናይዜሽን ፕሮጀከት አገልግሎት ከባንኩ በኪራይ የወሰደውን የእርሻ ትራከተር እና ማረሻ የማሽን የኪራይ እና የአገልግሎት ከፍያ በገባው ውል መሰረት ሊፈጽም ባለመቻሉ ምከንያት ባንኩ መልሶ የተረከባቸውንና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ ለመሸጥ ወይም ለማከራየት ይፈልጋል።
|
የተከራይሙሉ ስም |
በጨረታ የሚሸጠዉ (የሚከራየው) ንብረት ሁኔታ |
ጨረታዉ የሚካሄድበት |
የጨረታው ደረጃ |
||||
|
ዓይነት |
አድራሻ |
የጨረታው መነሻ ዋጋ |
ቀን |
ሠዓት |
ቦታ |
||
|
ሀርቨስት ሞደርን እርሻ መካናይዜሽን አገልግሎት ማህበር |
LANDINI 2022 MODEL 133HP Tractor፣ብዛት 01 |
በጋ/ሕ/ብ/ክ/መንግስት አኙዋ ዞን ፣ጋምቤላ ከተማ የዲስትሪከት |
ብር 7,265.379.06 |
ሐምሌ 15 ቀን 2018 ዓ.ም |
ከቀኑ 4፡00-5፡00 ስዓት |
ጋምቤላ ዲስትሪከት ቅጥር ግቢ ውስጥ ፣ሐምሌ15ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋቱ4፡00ሠዓት |
1ኛ ዝግ ጨረታ |
|
ማረሻ ናርዲ ባለ 5(አምስት)ዲስከ ብዛት 01 |
|||||||
|
መከስከሻ, AGRI-WAY ባለ 28 ምጣድ፣ ብዛት 01 |
|||||||
የጨረታው መመሪያ
1. ከላይ የተመለከቱትን ንብረቶች በጥሬ ገንዘብ መግዛት ወይም መከራየት የሚፈልግ ማንኛውም እካል (ግለሰቦች፣ ተቋማት ወይም አነስተኛና መካከለኛ ማህበራት) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የንብረቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/5(አንድ አምስተኛ) ጥሬ ገንዘብ ወይም በኢትዮጵያ ልማት ባንከ ስም በተዘጋጀና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በማስያዝ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
2. ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ(ካሽ) ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ ተጫራች ቀሪውን ገንዘብ በ15 ተከታታይ ቀናት ጊዜ ውስጥ አጠቃሎ መከፈል ይኖርበታል። ካልከፈለ የጨረታው ውጤት ተሰርዞ የተያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል፡፡
3. ላላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወይም ሲፒአ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
4. የጨረታው አሸናፊ ንብረቶቹን በጥሬ ገንዘብ ወይም እጅ በእጅ ሽያጭ የሚገዛ ከሆነ ተመሳሳይ ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መበት ከሌለው በመንግስት የሚጠበቁ ማናቸውንም ቀረጥና ሌሎች ከፍያዎች በቅድሚያ የመከፈል ግዴታ አለበት፡፡
5. የጨረታው አሸናፊ ባሸነፈው ዋጋ ላይ 15% /VAT/ ተጨማሪ እሴት ታከስ/ ጨምሮ የመከፈል ግዴታ አለበት፡፡
6. አሸናፊው ተጫራች ንብረቱን ለመከራየት የሚፈልግ ከሆነ ቢያንስ የማሽኑን ጠቅላላ ዋጋ 20 % በቅድሚያ በመከፈል በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የባንኩን የማሽነሪ ኪራይ መስፈርት በማሟላት የማሽነሪ ኪራይውል መፈረም ይኖርበታል ። በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ግዴታውን ካልተወጣ የጨረታው አሸናፊነት ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል፡፡
7. ንብረቶችን ከጨረታ በፊት ማየት ወይም መጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች በቅድሚያ ከባንኩ ጋር ፕሮግራም መያዝ ይኖርበቸዋል። ተጫራቾች ንብረቱን የሚገዙበትን ዋጋ ለዚህ ዓላማ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ሐምሌ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ሳጥኑ ሐምሌ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ይታሸጋል፡፡
8. ባንኩ የተሸለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
9. ለማንኛውም ማብራሪያ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪከት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር+241475512577/ +251475512588 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤሳ ዲስትሪክት
