Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Pipe Factory (APF) (የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ማህበር)
  • Address ባህር ዳር ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 09-35-98-37-29
  • Websitehttps://www.amharapipe.et/
  • Deadline29 Jun 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2026-06-29 14:30:00
  • Categories Plastic Raw Materials And Products

አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ የተለያዩ የፕላስቲክ ምርቶችን በብዛት እና በጥራት እያመረተ ለገበያ የሚያቀርብ ፋብሪካ ሲሆን ከሚያመርታቸው የምርት አይነቶች ውስጥ Geomembrane Sheet እና Common plastic Sheet የተባሉ ምርቶችን በብሔራዊ ግልፅ በጨረታ አወዳድሮ ከሐምሌ 01/2018 እስከ መስከረም 30/2019 ዓ.ም ድረስ መሸጥ ይፈልጋል፡፡


የምርት ሽያጭ ረታ ማስታወቂየ

የጨረታ ቁጥር:- APF/24/2018/Local

 

አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ የተለያዩ የፕላስቲክ ምርቶችን በብዛት እና በጥራት እያመረተ ለገበያ የሚያቀርብ ፋብሪካ ሲሆን ከሚያመርታቸው የምርት አይነቶች ውስጥ Geomembrane Sheet እና Common plastic Sheet የተባሉ ምርቶችን በብሔራዊ ግልፅ በጨረታ አወዳድሮ ከሐምሌ 01/2018 እስከ መስከረም 30/2019 . ድረስ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ እነዚህ ምርቶች ለተለያዩ የግብርና ስራዎች አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው

ሎት 1 Geomembrane Sheet ብዛት 1,200,000 ካሬ ሜትር ሲሆን ከዚህ ውስጥ

    ያልተበየደ ብዛት 1,020.000 .ሜ፣

    የተበየደ ብዛት 180,000 . ነው

    ለሽያጭ የቀረበው Geomembrane Sheet ምርት መልኩ ጥቁር (Dark Black) ሲሆን ውፍረቱ በአማካይ 0.4ሚሜ ነውይህ ምርት በጥቅል (Roll) የሚቀርብ ሲሆን

    ያልተበየደው የአንዱ ጥቅል ርዝመት 28 ሜትር ወርድ 6.25 ሜትር ሲሆን ስፋቱ 175 ካሬ ሜትር ነውየዚህ አንድ ጥቅል ምርት መነሻ የጨረታ ዋጋ ከነቫቱ ብር 228.57 ነው እንዲሁም

    የተበየደው የአንዱ ጥቅል ርዝመት 14 ሜትር ወርድ 12.5 ሜትር ሲሆን ስፋቱ 175.36 ካሬ ሜትር ነውየዚህ አንድ ጥቅል ምርት መነሻ የጨረታ ዋጋ ከነቫቱ ብር 230.00 ነው

ሎት 2 Common plastic Sheet ብዛት 1,358,626 ካሬ ሜትር ለሽያጭ የቀረበው Common plastic Sheet ምርት መልኩ ቢጫ (Light Yellow) ሲሆን ውፍረቱ በአማካይ 0.165 ሚሜ ነው ይህ ምርት በጥቅል (Roll) የሚቀርብ ሲሆን የአንዱ ጥቅል ርዝመት በአማካይ 130 ሜትር ወርድ 8.8 ሜትር ሲሆን ስፋቱ 1,144 ካሬ ሜትር ነው :: የዚህ አንድ ጥቅል ምርት መነሻ የጨረታ ዋጋ ከነቫቱ ብር 101.40 ነው:: ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን የጨረታ መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ (መወዳደር) ይችላሉ፡፡

 

1.     2018 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና ተያያዥ የሆኑ የሕጋዊነት ሠነዶችን ማለትም የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ቅጅ (Copy) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2.     ተወዳዳሪ ድርጅቶች ለተወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት በተናጠል የምርቱን ጠቅላላ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ጨምሮ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በፋብሪካው ስም በማሰራት ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሆኖም ግን የጨረታ ማስከበሪያው መጠን ለእያንዳንዱ ሎት ከብር 1,000,000 መብለጥ የለበትም፡፡

3.     ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመፈል ከፋብሪካው የፋይናንስ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 105 ማግኘት ይችላሉ፡፡

4.     ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን የሕጋዊነት ሠነዶቻቸውን ቅጅ (Copy) የመወዳደሪያ ዋጋቸውን፣ የጨረታ ማስከበሪያ እና ሌሎችን ማስረጃዎች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቢሮ ቁጥር 206 ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

5.     ጨረታው የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 10 ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 206 ከቀኑ 800 ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 830 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡ በጨረታው ፈቻ ዕለት የሚገኙት የተጫራች ድርጅቶች ተወካይ ወይም ባለቤት ህጋዊ የፍትሕ ልና ወይም የድርጅቱ ባለቤት ወይም ሠራተኛ ስለመሆኑ ከድርጀቱ የተፃፈ ደብዳቤ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው

6.     10ኛው ቀን ሕዝባዊ በዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡

7.     የውድድሩ አሸናፊ የሚለየው በየሎቱ ሲሆን በሎቱ ለተጠቀሰው ምርት ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች የውድድሩ ሸናፊ ይሆናል፡፡

8.     አሸናፊዎች ምርቱን ለማንሳት በቅድሚያ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታከስን ጨምሮ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና በፋብሪካው ስም በማሰራት ወይም በጥሬ ገንዘብ በማቅረብ አሸናፊነታቸው ከተገለጸበት እለት ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የውል ስምምነት የመፈፀም ግዴታ አለባቸው፡፡

9.     በየወሩ ማለትም በሐምሌ፣ በነሐሴ እና በመስከረም ወራት የሚነሳው የምርት መጠን Geomembrane Sheet እንደቅደም ተከተል 500,000 . 400,000 . 300,000 . ሲሆን Common plastic Sheet ደግሞ እንደቅደም ተከተለ 500,000 .ሜ፣ 429,313 .ሜ፣ 429,313 . ነው ስለሆነም የውድድሩ አሸናፊዎች ምርቱን ለማንሳት በቅድሚያ በየወሩ የሚያነሱትን ምርት ጠቅላላ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ጨምሮ 50% ውል በተያዘ 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ገቢ የማድረግ ግዴታ አለባቸው

10. ፋብሪካው ማንኛውንም ዓይነት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

11. ተጫራቾች ለሽያጭ የቀረቡትን ምርቶች በአካል በፋብሪካው አድራሻ በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ማየት ይችላሉ፡፡

12. ለበለጠ መረጃ 09-35-98-37-29/09-18-70-18-26/ 09 00-90-92-50 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

አማራ ፓይፕ ፋብሪካ /የተ/የግል ኩባንያ

ባህር ዳር

 

Save Tender