Tender Detail

Tender Details

  • Company HELVETAS Swiss Intercooperation
  • Address Mercy Plaza, 7th Floor, opposite Century Mall, Gurd Shola Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 251584175765
  • Websitehttps://helvetas-ks.org/
  • Deadline06 Jul 2026, 2:50 PM
  • magazineReporter Tenders
  • Bid Document Price
  • opening date2026-06-21 14:49:00
  • Categories Wood And Wood Working , Water Construction Machinery And Equipment

የሄልቬታስ-አፕ ውሜን ሀዋሳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር የወጣት ሴቶችና ልጃረዶችን ኑሮ ለማሻሻል የሚያግዝ የሼድ ጥገና በተዘጋጀው ዲዛይን መሠረት ጥቃቅን እና አነስተኛ በብረታ ብረት እና እንጨት ሥራ ዘርፍ ብቻ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ማህበራት መካከል ጨረታውን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡


ሼድ ጥገና ሥራ

የሄልቬታስ-አፕ ውሜን ሀዋሳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር የወጣት ሴቶችና ልጃረዶችን ኑሮ ለማሻሻል የሚያግዝ የሼድ ጥገና በተዘጋጀው ዲዛይን መሠረት ጥቃቅን እና አነስተኛ በብረታ ብረት እና እንጨት ሥራ ዘርፍ ብቻ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ማህበራት መካከል ጨረታውን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በሟሟላት መወዳደር ይችላሉ፡-

  1. በብረታ ብረት እና እንጨት ሥራ ዘርፍ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ማህበራት፤
  2. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ማህበራት፣
  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ እና የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ማህበራት፣
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ካስገቡት ጠቅላላ ዋጋ ከተጨ.እሴ.ታክስ ጋር 2% የጨረታ ማስከበሪያ በሄልቬታስ አካውንት ወጋገን ባንክ አካውንት ቁጥር 0863033111301 በማስገባት የባንክ ገቢ ማረጋገጨ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለበት ፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ የሄልቬታስ-አፕ ውሜን ሀዋሳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ቢሮ (ሀዋሳ ፒያሳ በሚኘው ንብ ህንፃ ስምንተኛ ፎቅ) በመቅረብ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 29_/10/2018 (06/07/2026) ተከታታይ የሥራ ቀናትንና ሠዓት በመጠቀም ብር 1000 /አንድ ሽ ብር / በመክፈል መግዛት ይችላሉ፤
  6. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦሪጂናልና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻልአንድ ኦሪጂናልና አንድ ኮፒ ቲክኒካል በአጠቃላይ አንድ ልቅ ኤንቬሎፕ ውስጥ በሰም በማሸግ እና በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስክ 29/10/2018 (06/07/2026) ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት በሥራ ቀንና ሠዓት በሄልቬታስ-አፕ ውሜን ሀዋሳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት (ሀዋሳ ፒያሳ በሚኘው ንብ ህንፃ ስምንተኛ ፎቅ) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  7. ጨረታው በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከቀኑ30 ሠዓት በሄልቬታስ-አፕ ውሜን ሀዋሳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት (ሀዋሳ ፒያሳ በሚኘው ንብ ህንፃ ስምንተኛ ፎቅ ፎቅ) ይከፈታል፡፡
  8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር 0939064059/0911331955

የሄልቬታስአፕ ውሜን ሀዋሳ ፕሮጀክት /ቤት

ሀዋሳ

Save Tender