በወላይታ ሶዶ ከተማ የሚገኘው የደቡብ ኢትዮጵያ ከልል መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ ለ2019 በጀት ዓመት በከተማ ውስጥ ከሚገኙ ጋራዦች የተሽከርካሪ ዓመታዊ ጥገና አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ 01/2019
በወላይታ ሶዶ ከተማ የሚገኘው የደቡብ ኢትዮጵያ ከልል መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ ለ2019 በጀት ዓመት በከተማ ውስጥ ከሚገኙ ጋራዦች የተሽከርካሪ ዓመታዊ ጥገና አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይኖርባችኋል።
1. በሚወዳደሩበት ዘርፍ አግባብነት ያለውና ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. በፈዴራል ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጄንሲ ዌይብ ሳይት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ከዌይብ ሳይት አትመው ከጨረታ ሰነድ ጋር ማያያዝ የሚችሉ ወይም በከልሎች በአቅራቢነት ስለመመዝገባቸው የእቅራቢነት የምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
3. የግዥው መጠኑ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ለተጨማሪ እሴት ታከስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለተጫራቾች ከፍት ሆኖ ይቆያል።
5. ተጫራቶች, ጨረታው ከፍት ሆኖ በሚቆይበት ጊዜ ውስጥ በቢሮው የተዘጋጀውንና የጨረታውን ዝርዝር ሁኔታ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ የንግድ ፈቃዳቸውን በማሳየት ዘወትርበሥራ ሰዓት በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቀርበው የማይመለስ ብር 300.00/ሦስት መቶ ብር/ በመከፈል መውሰድና የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በአግባቡ በማዘጋጀት በፖስታ አሽገው ጨረታው ለተጫራቾች ከፍት ሆኖ በሚቆይበት ቀን እስከ 11፡25 ሰዓት ድረስ በቢሮው ቅጥርግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ጨረታው ከፍት ሆኖ በሚቆይበት የመጨረሻው ቀን 11፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ቀጥሎ ባለው 16ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ይከፈታል። 15ኛው እና 16ኛው ቀን የሚውለው ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓላት ቀን ላይ ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በ3፡00 ሰዓት ተዘግቶ 3፡30 ሰዓት ይከፈታል።
7. ተጫራቾች የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥትፋይናንስ ቢሮስም ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን ብር 30,000.00 በሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንከ የተረጋገጠ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
8. የፋይናንሻል የቴከኒክ ሰነድ እና የሲ.ፒ.ኦ ፖስታ ተለይቶ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጨረታው አየር ላይ መቆያ ጊዜ ከሚያበቃበት የመጨረሻው ቀን ጀምሮ ላሉት ለ60 ተከታታይ ቀናት የሚያገለግል መሆን ይኖርበታል።
9. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸበት በ05 ቀናት ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ በመያያዝ በ15 ቀናት ውስጥ ውል መግባት የሚችሉ መሆን አለበት።
10. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
1. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 046-180-50-71 በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን
2. እንገልጻለን።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ
