Tender Detail

Tender Details


የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በአዋጅ ቁጥር 1090/2010 እና በሚኒስተሮች ደንብ ቁጥር 425/2010 መሰረት ያገለገሉ የኤክትሪክ እና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ . ሩሀአዲ/ግዳ/025/2018

 

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በአዋጅ ቁጥር 1090/2010 እና በሚኒስተሮች ደንብ ቁጥር 425/2010 መሰረት ያገለገሉ የኤክትሪክ እና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡

1-    በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸውና ከአካባቢ ደን የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡

2-    ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ የግብር መለያ ሰርተፊኬት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው።

3-    የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመከፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 19 ቀን 2018 . ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለገሃር በሚገኘው የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት 1 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

4-    ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ መነሻውን 20% (ሃያ በመቶ) ሲሆን ዝቅተኛው የማስያዣ ዋጋ ብር 500.00(አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ መድን ድርጅት (Ethiopian Insurance Corporation) በሚል ሥም የጨረታ ማስከበሪያ በባንከ ከፍያ ማዘዣ (CPO) አዘጋጅተው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡

5-    ተጫራቾች ለአንድ ዓይነት ወይም ከአንድ በላይ ለሆኑ ዕቃዎች መጫረት ይችላሉ፡፡

6-    ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ የሆነበትን የዕቃ ዓይነት አጠቃላይ ዋጋውን በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ በመክፈል በአለበት ሁኔታ ተረከበው መውሰድ አለባቸው፡፡ከፍያውን ፈፅመው ንብረቶቹን በተገለፀው ጊዜ የማያነሱ ተጫራቾች የጥበቃ ወጪ በቀን ብር 100.00(አንድ መቶ ብር) ይከፍላሉ፡፡

7-    ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ከገዛ በኋላ ዕቃዎቹን ሳሪስ ንፋስ ስልክ ቀለም ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የድርጅቱ ግቢ መጋዘን በመሄድ ሰኔ 18 እና ሰኔ 19 ቀን 2018 ከጠዋቱ 230 እስከ 600 ድረስ ሰነዱን የገዙበትን ደረሰኝ በመያዝ መመልከት ይችላሉ፡፡

 

8-    ተጫራቾች መወዳደሪያ ሠነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ሰኔ 27 ቀን 2018 .. እስከ ቀኑ 800 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ማለትም ሰኔ 27 ቀን 2018 .. 830 ሰዓት በግዥ ዳይሬክቶሬት የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

9-    ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት -

 

 

Save Tender