የአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቤቶች መሸጥ ይፈልጋል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በፍርድ ባለ መብት አቶ ተፈሪ ዘነበ እና በፍርድ ባለ እዳ አቶ አበበ ወጋየሁ መካከል ያለውን የአፈፃፀም ክስ ክርክር በ1ኛ ስፋቱ 480 ካሬ ሜትር የሆነ የካርታ ቁጥሩ 624/91 የሆነ በቀን 03/13/2003 የሆነ የጨረታ መነሻ ብር 7,585,776(ሰባት ሚሊየን አምስት መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ሰባት መቶ ሰባ ስድስት) እና 2ኛ ስፋቱ 193 ካሬ ሜትር የሆነ ካርታ ቁጥሩ 40/2002 በቀን 25/04/2003 የጨረታ መነሻ ዋጋ 1,291,882.17(አንድ ሚሊየን ሁለት መቶ ዘጠና አንድ ሺህ ስምንት መቶ ሰማንያ ሁለት ከ17/100) የሆነ በፍርድ ባለ እዳ ስም ተመዝግቦ በአዳማ ከተማ አስተዳደር አባ ገዳ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኝ ቤቶች ሲሆን በአጠቃላይ የጨረታ መነሻ ብር 8,877,658.17(ስምንት ሚሊየን ስምንት መቶ ሰባ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ሀምሳ ስምን ሺህ ብር ከ17/100) የሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሕግ አንቀጽ 423/1 እና 2/፣ 425 (1 እና 2) እና 426 መሠረት የመነሻ ጨረታ ዋጋ በሆነ ከመነሻ ዋጋ ውስጥ 1/4 ሲፒኦ በማስያዝ ቤቱ በሚገኝበት ቦታ ጨረታ በቀን 18/11/2018 የካርታ ቁጥር 624/91 የሆነ በቀን 03/13/2003 የተሰጠ ቤት ከሰዓት በፊት ከ3፡30 እስከ 6፡30 ሰዓት እና የካርታ ቁጥር 40/2002 የሆነ በቀን 25/04/2003 ዓ/ም የተሰጠ ደግሞ ከሰዓት በኋላ ከ8፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ጨረታው ተካሂዶ ስለሚሸጥ መግዛት የሚፈልግ አካል ጨረታ ተጫርቶ መግዛት የሚችል መሆኑን የአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍረድ ቤት አዟል።
የአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት
