የንግድ ቤት ጨረታ ማስታወቂያ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የፍርድ ባለመብት አቢሲኒያ ባንክ አዳማ ዲስትሪክት እና የፍርድ ባለዕዳዎች 1ኛ ዘመናይ ከበደ፣ 2ኛ ካፕቴን ሽመልስ ከበደ፣ 3ኛ መስፍን ከበደ እና 4ኛ አድነው ከበደ መካከል ያለው የፍርድ አፈፃፀም ክርክር አስመልክቶ የአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጨረታ ማስታወቂያ የቅይጥ ንግድ ቤት ካርታ ቁጥሩ 1133/92 የሆነ በእልፍነሽ መንገሻ ስም ተመዝግቦ በአሰላ ከተማ አስተዳደር ሀንቁ ቀበሌ ውስጥ የሚገኝ የጨረታ መነሻ ዋጋ ግምት ብር 4,018,793.86 (አራት ሚሊዮን አሥራ ስምንት ሺህ ሰባት መቶ ዘጠና ሦሥት ከ86 ሣንቲም) በሆነ በፍ/ሥ/ሥ/ህ አንቀጽ 423(1 እና 2) ፣ 425(1 እና 2) እና 426 መሠረት ለመሸጥ ስለሚፈልግ መግዛት የሚፈልግ አካል ሲፒኦ የመነሻ ግምት ሃያ አምስት መቶኛ (25%) ወይም 1/4ኛ በማስያዝ ቤቱ የሚገኝበት ቦታ አሰላ ከተማ ሀንቁ ቀበሌ መሆኑን አውቃችሁ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 17/10/2018 እስከ 17/11/2018 ሰላሳ (30) ቀን አየር ላይ የሚቆይ መሆኑ እና ይህንን ንብረት መግዛት የምትፈልጉ ሰዎች በ18/11/2018 ከ3፡30 እስከ 6፡30 ድረስ የሚካሄድ መሆኑን አውቃችሁ ቀርባችሁ እንዲትገዙ የአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያሳውቃል።
የአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት
