ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር በስሩ ለሚገኝ ለሻሎ የእንሰሳት መኖ ማቀነባበሪያ ግብዓት የሚሆን ስጋ እና አጥንት በግልጽ ጨረታ ብቃቱ ያላቸውን ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለስድስት ወራት የሚሆን 4800 ኩንታል ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር EL/LP-05/2026
ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር በስሩ ለሚገኝ ለሻሎ የእንሰሳት መኖ ማቀነባበሪያ ግብዓት የሚሆን ስጋ እና አጥንት በግልጽ ጨረታ ብቃቱ ያላቸውን ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለስድስት ወራት የሚሆን 4800 ኩንታል ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች:-
በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ እና የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ ማስረጃ ኮፒ ማያያዝ አለበት።
ተጫራቹ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለበቸው።
ምርቱን ለመግዛት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች በጨረታ መመሪያ ላይ በተገለፀው መሰረት ይሆናል።
ተጫራቾች በጨረታው ለማሳተፊ የሚያስችላቸውን የጨረታ ማስከበሪያ ብር500,000.00 በሲፒአ ወይም በሁኔታዎች ያልተመሰረተ የባንከ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርበታል።
የጨረታውን አሸናፊ የሆነው ድርጅት ለመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና የግዥውን ጠቅላላ ዋጋ 10% በሲፒአ ወይም በሁኔታዎች ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርበታል።
አሸናፊው የሚኖረው መብትና ግዴታዎች በውል ውስጥ የሚካተቱ ይሆናል።
ተጫራቾች ድርጅቱ በሚያቀርበው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የመወዳደሪያ ዋጋቸውን መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጠበት ቀን ጀምሮ ከሰኞ እስከ አርብ ዘወትር በስራ ሰአት ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ ላምበረት አካባቢ በሚገኘው የአቅርቦት መምሪያ በስራ ሰዓት በመምጣት የማይመለስ 200.00 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ሰነዳቸውን ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰአት ጨረታው በዚሁ እለት ታሽጎ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ላምበረት በሚገኘው የኤልፎራ ህንጻ 8ኛ ፎቅ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይካሄዳል::
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልከ ቁጥር 0116461076/0976806076/0911330099 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የኤስፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማ
