ዘኔቸር ኤንድ ባዩዳይቨርሲቲ ኮንሰርቬሽን ዩኒዬን ኢትዮጵያ (The Nature and Biodiversity Conservation Union Ethiopia) የደቡብ ምዕራብ ክልል ጽ/ቤት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በካፋ እና በቤንች ሸኮ ዞንኖች በሚገኙ ወረዳዎች እየተገበረ ላላቸዉ ForestConnect እና Wetland Management ፕሮጀክቶች ለሚደገፉ ተጠቃሚዎች የሚሰራጭ 860 ኬንያ ቶፕ
የንብ ቀፎ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
ዘኔቸር ኤንድ ባዩዳይቨርሲቲ ኮንሰርቬሽን ዩኒዬን ኢትዮጵያ (The Nature and Biodiversity Conservation Union Ethiopia) የደቡብ ምዕራብ ክልል ጽ/ቤት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በካፋ እና በቤንች ሸኮ ዞንኖች በሚገኙ ወረዳዎች እየተገበረ ላላቸዉ ForestConnect እና Wetland Management ፕሮጀክቶች ለሚደገፉ ተጠቃሚዎች የሚሰራጭ 860 ኬንያ ቶፕ ባር የተሰኘ የንብ ቀፎ ከህጋዊ አምራቾች/አቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት ከታች የተቀመጠውን ዝርዝር መስፈርት የምታሟሉ ህጋዊ አምራቾች/አቅራቢዎች የምርት መግለጫ (Product Specification) ላይ በተቀመጠዉ መሰረት ቫትን ጨምሮ የአንዱን ቀፎ መሸጫ በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ (Proforma) ሞልታችሁና በኤንቬሎፕ አሽጋችሁ ቦንጋ ከተማ ብሔራዊ ቡና ሙዚዬም ከፍ ብሎ በሚገኘው የናቡ ኢትዮጵያ ደ/ም/ኢ/ጽ/ቤት ወይንም ቤንች ሽኮ ዞን ሚዛን-አማን ከተማ አቶ ሰይድ ህንጻ ላይ በሚገኘው የድርጅታችን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከቀን 17/10/2018ዓ.ም እስከ 23/10/2018ዓ.ም በሥራ ሰዓት ዉስጥ እንድታስገቡ እያሳሰብን ጨረታዉ በቀን 26/10/2018ዓ.ም ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በቦንጋ ከተማ በሚገኘው የናቡ ኢትዮጵያ ደ/ም/ኢ/ጽ/ቤት የሚከፈት መሆኑንን እንገልጻለን።
በጨረታውን ለመወዳደር መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
1. የ 2018 ዓ.ም የታደስ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለዉ፣
2. የዘመኑን ግብር የከፈለ፣
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ የሆነ፣
4. ለሚከፈለው ገንዘን ሕጋዊ ደረሰኝ መስጠት የሚችል
5. ከላይ የተጠቀሱትን ህጋዊ ሰነዶች ኮፒ ከጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል፤
ማሳሰቢያ፡-
· የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ከሰኔ 18-23/2018 ዓ.ም ባሉት አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል
· ተጫራቾች ከላይ በቁጥር የተጠቀሰዉን የቀፎ መጠን ሰርተዉ ለተቋሙ የሚያስረክበብትን ጊዜ በጨረታዉ ዋጋ ማስገቢያ ሰነድ ዉስጥ መግለጽ አለባቸዉ
· ከዚህ ቀደም ለተለያዩ ተቋማት ጥራቱን የጠበቀ የንብ ቀፎ ውል በገባበት ጊዜ ውስጥ በማስረከብ የእውቅና ሰርተፍኬት ያለው አቅራቢ ስርተፍኬቱን ማያያዝ ይጠበቀበታል።
· ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የሚገዛው የኬኒያ ቶፕ ባር ቀፎ ዝርዝር የምርት መግለጫ (Product Specification)
ሀ. እያንዳንዱ የንብ ቀር የሚሰራው ከበሰለና በደንብ ደርቆ ከወጣለት የዋንዛ እንጨት ይሆናል: በተጨማሪም፡-
1. ቀፎው የሚሰራበት ጣውላ በምንም ዓይነት ተሕዋስያን፤ ተባይና ነፍሳት ያልተጠቃ መሆን አለበት፣
2. ጣውላው ያልተሰነጣጠቀ፣ ቋር የሌለበትና ምንም ዓይነት ቀዳዳ የማይታይበት መሆን ይኖርበታል።
ለ. የሚሰራው የኬንያ ቶፕ ባር የንብ ቀፎ ዲዛይንና መጠን የተለያዩ ክፍሎች እንደሚከተለው ነው።
የቀፎው መጠን
1. ርዝመት 1 ሜትር
2. የላይኛው ጎን ስፋት 40 ሳ.ሜ
3. የታችኛው ጎማ ስፋት 22 ሳ.ሜ
4. ከፍታ 30 ሳ.ሜ
5. የቀፎ ክዳን (Root) ስፋቱ 60 ሳ.ሜ፣ ርዝመቱ 120 ሳ.ሜ ሆና ውፍረቱ 2 ሳ.ሜ በሆነ ጣውላ የሚሰራ ሲሆን በልሙጥ ፐርሊን ቆርቆሮ መሸፈን አለበት።
የቀፎው ዲዛይን
ከታች በምስሉ ላይ እንደተመለከተው ሲሆን የጎን ግድግዳዎች ወይም ጣውላዎችና መወጠሪያዎች በምስሉ መሰረት ርቀታቸውን ጠብቀው የሚሰሩ ይሆናል። በአንደኛው የቀፎው ፊት የታችኛው ክፍል የንቦች መግቢያ በር ይኖረዋል።
ሐ. የቀፎ ርብራቦች (Frames) ለአንድ ቀፎ በድምሩ 30 ሲሆኑ እያንዳንዱ ርብራብ (Frame) ስፋቱ 3.2 ሴንቲ ሜትሮ፣ ውፍረቱ 2 ሴንቲ ሜትር ሆኖ መሃሉ ለስም መቀቢያ የሚሆን መስመር (Wax starter strip) ሊኖረው ይገባል። ተጨማሪ ማብራሪያዎች በባለሙያ የሚሰጡ ይሆናል።
መ. ኬንያ ቶፕ ባር የንብ ቀፎ ተገጣጥሞ ሲታይ ከታች በምስሉ እንደሚመለከተው ሆኖ አራቱም የጎን ግድግዳዎች ከውጭ በኩል ቢጫ ቀለም መቀባት አለባቸው። እንደዚሁም በአንዱ በኩል ባለው የግድግዳው ፊት መሃል ላይ የንቦች መውጫና መግቢያ በር ኖሮት ለንቦች መወጣጫ የሚሆን አነስተኛ ጣውላ በምስሉ ላይ በሚታየው መሰረት መኖር አለበት።
