በቂሊንጦ ቀጠሮ ማረፊያ ማዕከል ለህብረት ሱቅ እና መዝናኛ ከበባት አገልግሎት የሚውሉ አቅርቦቶችን ማለትም የተፈጨ ቡና፣ የለውዝ ቅቤ፣ የሻይ ቅጠል፣ የዳቦ ዱቄት፣ የዳቦ እርሾ፣ የዳቦ ማኮፈሻ፣ ጨው፣ የምግብ ዘይት፣ የወጥ ማጣፈጫ ቅመም፣ ፕላስቲክ እሽግ ጁስ ባለ፣ ፕላስቲክ እሽግ ማር፣ እሽግ ውሃ፣ ኢንዶሚን፣ ወተት፣ እርጎ፣ ዱቄት ወተት፣ ገብስ ቆሎ፣ ማርማራታ፣ ማርጋሪን፣ የአሳ ሰርዲን የዶሮ ዕንቁላል
የጨረታ ማስታወቂያ
በቂሊንጦ ቀጠሮ ማረፊያ ማዕከል ለህብረት ሱቅ እና መዝናኛ ከበባት አገልግሎት የሚውሉ አቅርቦቶችን ማለትም የተፈጨ ቡና፣ የለውዝ ቅቤ፣ የሻይ ቅጠል፣ የዳቦ ዱቄት፣ የዳቦ እርሾ፣ የዳቦ ማኮፈሻ፣ ጨው፣ የምግብ ዘይት፣ የወጥ ማጣፈጫ ቅመም፣ ፕላስቲክ እሽግ ጁስ ባለ፣ ፕላስቲክ እሽግ ማር፣ እሽግ ውሃ፣ ኢንዶሚን፣ ወተት፣ እርጎ፣ ዱቄት ወተት፣ ገብስ ቆሎ፣ ማርማራታ፣ ማርጋሪን፣ የአሳ ሰርዲን የዶሮ ዕንቁላል፣ በሶ፣ ዳቦ ቆሎ፣ አፕል፣ ሙዝ፣ ማንጎ፣ አቮካዶ፣ ብርትኳን፣ ፓስታ፣ ማካሮኒ፣ አተር፣ ባቄላ፣ ምስር፣ ሩዝ፣ ዛላ በርበሬ፣ ቸኮሌት፣ | ከረሜላ፣ ማስቲካ የገላ ሳሙና፣ የልብስ ሳሙና፣ ፈሳሽ ሳሙና፣ አይጃከስ፣ የዱቄት ሳሙና፣ የፀጉርቅባት፣ የፊት ክሬሞች፡ ሎሽን፣ ቫዝሊን፣ ሻምፖ፣ ዶድራንት፣ የጥርስ ብሩሽ የጥርስ ሳሙና፣ የፂም መላጫ፣ የጥፍር መቁረጫ፣ ነጠላ ጫማ፣ ደብተር፣ እስክሪቢቶ፣ ልሙጥ ወረቀት፣ የሻይ ማሽን፣ የወንዶች የፀጉር ማሽን፣ የማቀዝቀዣ ፍሪጅ እና የመሳሰሉትን ሸቀጣ ሸቀጦች አወዳድሮ በውል መግዛት ይፈልጋል።
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የሚከተሉትን መመሪያና መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
1, በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን፣ በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው የተገለፀ መሆን አለበት::
2. የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ::
3. የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉና የታደሰ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው::
4. የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል አቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው እንዲሁም በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከገቢዎች ጉምሩክባለስልጣን የዘመኑን ግብር ከፍለው ስለማጠናቀቃቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው::
5 ከደረጃ መዳቢዎች የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
6. ጥቃቅንና አነስተኛ ከሆኑ በጨረታው ለመሳተፍ ከአደራጃቸው አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው::
7.የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 150.00/አንድ መቶ ሃምሳ⁄ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቀጠሮ ማረፊያ ማዕከል ስም በአካውንት ቁጥር1000029497498 ገንዘቡን ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ስራ ክፍል ቢሮ ቁጥር21 መግዛት ይችላሉ::
8. ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችና የዋጋ ማቅረቢያዎችን ፋይናንሻል ሰነዶችን በተለያዩ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለበት፡፡
9. ቴከኒካልና ፋይናንሽል ሰነድ በአንድ ላይ አሽጎ ያቀረበ ተወዳደሪ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታው ውጭ ይደረጋል::
10. ማንኛውም ተጫራቾች የሚያስገቡት ሰነድ ቴከኒካል ሰነድ ኦርጅናሉን እና ኮፒውን ለየብቻ በተለያዩ ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የሚጫረቱበትን የጨረታ ሰነድ ቁጥር በትከከል መፃፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ እና በሁሉም የመጫረቻ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ማህተም በመምታት ማስገባት ያለባቸው ሲሆን ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ሰነድ፤ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የለውም::
11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያስይዙት ሲ ፒ ኦ ከቴከኒካል ሰነዶች ከአርጅናሉ ጋርበአንድ ለይ አሸገው ማቅረብ አለባቸው::
12, ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000/ሃያ አምስት ሺህ ብር / በባንክ በተረጋገጠ CPO በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቀጠሮ ማረፊያ ቤት ስም አዘጋጅተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው በታሽገ ፖስታ እስከ ሰኔ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 21 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው እንዲሁም የባንከ ዋስትና የሚያስይዙ ተጫራቾች የቆይታ ጊዜው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 90 ቀንና ከዚያ በላይ መሆኑ ይኖርበታል::
13. ጨረታው ሰኔ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች /ወኪሎቻቸው/በተገኙበት ቂሊንጦ በሚገኘው በመ/ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል::
14. ሆኖም ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ሳይገኙ ቢቀሩ ጨረታው አይስተጓጎልም ወይም ውድቅ አይሆንም፡፡
15. የጨረታው ዝርዝር መመሪያ በጨረታ ሰነዱ ተዘርዝሮ ቀርቧል::
16. አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም እንዲሁም ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም :
17. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
18. ጨረታው በሚከፈትበት ቀን የአመት በዓላት ወይም በተለያዩ ምክንያቶች ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ጨረታው ይከፈታል።
አድራሻ፡- ቂሊንጦ ቀጠሮ ማረፊያ ማዕከል አ/አ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አጠገብ ስበስጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0114522778 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
የቂሊንጦ ቀጠሮ ማረፊያ ማዕከል
