ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን የአርሲ ሀገረ ስብከት ልማት መርሃ ግብር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በኦሮሚያ ክልል በጢቾ ወረዳ ጢቾ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን የመፀዳጃ ቤት ግንባታ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ መሠረት ደረጃቸው 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ጠቅላላ ወይም የህንፃ ሥራ የግንባታ ፈቃድ ያላቸውንና የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የመፀዳጃ ቤት ግንባታ ሥራ ጨረታ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን የአርሲ ሀገረ ስብከት ልማት መርሃ ግብር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በኦሮሚያ ክልል በጢቾ ወረዳ ጢቾ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን የመፀዳጃ ቤት ግንባታ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ መሠረት ደረጃቸው 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ጠቅላላ ወይም የህንፃ ሥራ የግንባታ ፈቃድ ያላቸውንና የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
- ደረጃቸው GC/BC 7 እና ከዚያም በላይ ያላቸውና ፈቃዳቸውን ለ2017 ዓ.ም ያሳደሱ፣ የመንግስት ግብር የከፈሉና 6 ወር ያላለፈው የግብር ክሊራንስ የሚያቀርቡ፣ የኮንስትራክሽን ሚ/ር ወይም ቢሮ የምዝገባ ሰርቲፊኬት፣ ቫት፣ ቲን፣ ግብር የከፈሉበትን ክሊራንስና ሌሎች ማስረጃዎችን ማቅረብ የሚችሉ፤
- ከዚህ በፊት ለሰሩት ቀጥተኛ ተዛማጅነት ያለው የህንፃ ግንባታ ሥራ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ቢያንስ ሁለት ማስረጃ የሚያቀርቡ፤
- ጠቅላላ ሥራውን በ60 ቀናት አጠናቀው የሚያስረክቡ፤
- ለሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ ከአርቲሜቲክ በኋላ የሚሰላ 2 በመቶ እውቅና ካለው ባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ከአሁን ቀደም በድርጅታችንም ሆነ በክልሉ ክስ የሌለበት፤
- የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት አሰላ ከተማ ከሚገኘው የማስተባበሪያው ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፣
- ተጫራቾች የሞሉትን ዋጋ ዋናውን ከሲ.ፒ.ኦ ጋር እና ፎቶ ኮፒውን ለብቻው ዕንዲሁም አስፈላጊ ቴክኒካል ሰነዶችን ኮፒና ኦርጂናል ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ 10ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በእለቱ ከረፋዱ በ4፡30 ሰዓት በማስተባበሪያው ጽ/ቤት መገኘት የፈለጉ ተጫራቾች እና የጨረታ ኮሚቴ በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 10ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡ኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን አሰላ ከተማ ቀበሌ 11 /አርዱ
ስልክ፡ 0912247019 መደወል ይቻላል
