Tender Detail

Tender Details


የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኮፐር(መዳብ) እና በብረት መልክ የሚወገዱንብረቶች ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር ኢኤስ/ንአ/ግጨ-10/2018

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

.

የሚወገደው ንብረት ዓይነት

የሚገኝበት

መስኪያ

ብዛት

የጨረታ ማስከበሪያ (CPO)

የጨረታ መዝጊያ

የጨረታመክፈቻ

1

ኮፐር(መዳብ)

ኮተቤ

ኤሌክትሪካል ወርክ ሾፕ

በኪ.

8,500

290,000

ሐምሌ 07 ቀን 2018 .

8:00

ሐምሌ 07 ቀን 2018 .

ከቀኑ 800

2

 

በብረት መልክ የሚወገዱ

50,000

100,000

ሐምሌ 07 ቀን 2018 . ከቀኑ

8:00

ሐምሌ 07 ቀን 2018 .

ከቀኑ 800

 

ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ውድድሩ የሚከናወነው ሙሉ በሙሉ በአክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበርበፈጠሩት የማወዳደሪያ ሲስተም መተግበሪያ auction.et መሰረት መሆኑን እየገለጽን፤ መስፈርቶቹ ከዚህ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-

1.     በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ወይም የታደሠ መታወቂያ ሊኖራቸው ይገባል፡፡

2.     ስለጨረታው አካሄድ እና ንብረቶች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ የኦከሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ በነጻ አውርደው መመልከት ይችላሉ።

3.     ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አክሽን ኢትዮጵያ አከሲየን ማህበር ጋር ቀጠሮ በማስያዝ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 300 እስከ 1000 ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ በመገኘት መመልከት ይቻላል፡፡

4.     ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዋጋ 15% ቫትን ጨምሮ ማቅረብ አለባቸው፡፡

5.    ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና(Bid Security) በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስም ... በማሰራት የአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ

1.     የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ፡፡

6.     ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች የጨረታውን ሂደት በቀጥታ (online) መከታተል ይችላሉ፡፡

7.     ተጫራቾች የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (action.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ።

8.     በጨረታው አሸናፊ ለምትሆኑ ተጫራቾች ለወደፊት አሸናፊነታችሁ ከሚገለፅበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የአሸነፉችሁበትን ዋጋ ሙሉውን ከፍያ ለወደፊት በምናሳውቃችሁ በተቋማችን ሂሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ የሽያጭ ውል ስምምነት የመፈጸም ግዴታ ይኖርባችኋል፤ ሆኖም ግዴታቸውን የማይወጡ ተጫራቾች ለወድድርያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ... ለተቋማችን ገቢ ይደረጋል፡፡

9.     ከላይ የተጠቀሰውን እና በጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጡ መመሪያዎችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ሊደረግ ይችላል፡፡

10.                        ተቋሙ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

11.                        የኦከሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልከ መስመር09-05-11-55- በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

12.                        ንብረቶቹን በተመለከተ በስልክ ቁጥር 011-1-11-98-97 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት

Save Tender