ገዳ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/1992 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን ከታች በሰንጠረዡ የተገለጸውን ቤት ባለበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የሐራጅ ማስታወቂያ
ቁጥር፡- 003/3/2018
ገዳ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/1992 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን ከታች በሰንጠረዡ የተገለጸውን ቤት ባለበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
|
የተበዳሪው ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
ለጨረታ የቀረበው ንብረት ዓይነት |
አበዳሪው ቅርንጫፍ |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻና የቦታ ስፋት |
የጨረታ መነሻ ዋጋ
|
የጨረታዉ ቀንና ሰዓት |
ጨረታው የወጣው |
||||
| ከተማ | ቀበሌ/ወረዳ | የባለቤትነት መረጋገጫ ቁጥር | የቦታ ስፋት በካ.ሜ | ቀን | ሰዓት | ||||||
| ሪኖ ዋን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ | አቶ ናሆም ዳዊት ሀሰን | የመኖሪያ ቤት | ዶሎ ቢዴና | ቢሾፍቱ ከተማ ድባዩ ክ/ከተማ | ደካ ቦራ | OR003074513013 | 109.14 | 12,094,783.00 | 25/11/2018 | 3፡0-4፡00 | ለሁለተኛ ጊዜ |
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ/ሲ.ፒ.ኦ አሰርተው ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል፡፡
- ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ባለዕዳዎቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ ጎተራ ወንጌላዊት ህንፃ አከባቢ በሚገኝ ገዳ ባንክ ህንፃ 7ኛ ፎቅ ላይ ይካሄዳል፡፡ በዕለቱ ባለ ዕዳዎች እና ታዛቢዎች ባይገኙም ጨረታው ይካሄዳል፡፡
- ድርጅቶች ጨረታው ላይ ለመሳተፍ ተረጋግጦ የተመዘገበ የመመስረቻ ፅሁፍ እና እንደአስፈላጊነቱ መተዳደሪያ ደንብ እና ቃለ-ጉባኤዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጅ መዝጊያ በፊት ይጠናቀቃል፡፡ የጨረታ መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ ከፍተኛ ዋጋ የሰጠ ተጫራች ካልተለየ አስኪለይ ድረስ ጨረታው የሚቀጥል ይሆናል፡፡
- በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ከባንኩ የህግ አገልግሎት መምሪያ ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች አሸናፊ መሆኑ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ ለባንኩ አጠቃሎ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ የማያደርግ የጨረታ አሸናፊ ያስያዘው ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚፈጠረው ልዩነት ይጠየቃል፡፡
- ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ንብረቱን በማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች ግብር፣ የሊዝ ክፍያ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የስም ማዛወሪያ እና ማናቸዉም ከጨረታው ጋር በተገናኘ መንግስት የሚጠይቀውን ክፍያ ይከፍላል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ በንብረቱ ላይ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ የሚከፈለውን ክፍያ ለመክፈል ንብረቱ በሚገኝበት ወረዳ ወይም ከተማ አስተዳደር በመቅረብ የሊዝ ውል መዋዋል አለበት፡፡
- ተጨራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች በስራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዘው ለመጎብኘት ይችላሉ፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0920885734 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ባንኩ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
