Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ
  • Address ቶታል ሶስት ቁጥር ማዞሪያ 300 ሜትር ከፍ ብሎ ተዘነኦ ሆስፒታል አጠገብ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115579684
  • Websitehttps://etsugar.com/esig/
  • Deadline15 Jul 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price300.00
  • opening date2026-07-15 10:30:00
  • Categories Steel, Metals And Aluminium , Metals And Metal Working

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ስኳር ኢዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ከግንባታ የተራረፉ ቁርጥራጭ ብረታ ብረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የሽያጭ ጨረታ ቁጥር- አሸጨ 001 /ኦኩስፋ /-2/2018

 

በኢ... ስኳር ኢዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተጠቀሰውን ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ሎት 1 - ከግንባታ የተራረፉ ቁርጥራጭ ብረታ ብረት 100 ቶን ሸያጭ ጨረታ

ስለዚህ፡-

1.     በዘርፉ የተሰማራችሁና በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ የቫት ምዝገባ ሰርተፊኬት እንዲሁም የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።

2.     በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሁለት መቶ ብርበመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ) ከሰዓት በፊት 230 – 600 ከሰዓት በኋላ 700-1030 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት 230 – 600) ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

3.     ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኤምቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህበባንክ የተመሰከረለት (CPO) ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

5.     ተጫራች ለተጫረተው ዕቃ መነሻ ዋጋ መሰረት ለመግዛት በቂ አቅም መኖሩን ለማረጋገጥ የባንክ ስቴትመንት ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

6.     ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ተዘግቶ 430 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።

7.     ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 60 ቀናት ነው።

8.     የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታው ዋጋ ጸንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለተከታታይ 60 ቀናት ነው።

9.     የዕቃው ርክክብ የሚፈፀመው ኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካ የሚገኝበት ማለትም ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ኃይል ውሃ ቀበሌ ነው።

10.ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11.የጨረታው ሰነድ የሚሸጥበት የሚገባበትና የሚከፈትበት አድራሻ ቀጥሎ የተመለከተው ይሆናል።

አድራሻ፡- ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ማስተባበሪያ /ቤት አዲስ አበባ ነው።

ለበለጠ መረጃ ይህንን የስልክ ቁጥር መጠቀም ይቻላል 09 91 14 94 85 / 09 40 20 94 64

 

በኢ... ስኳር ኢዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ

Save Tender