በኢፌዲሪስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተጠቀሰው ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ
የሽያጭ ጨረታ ቁጥር- አሽጨ 001/ኦኩስሩ/9-2/2018
በኢፌዲሪስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተጠቀሰው ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ሎት 1 - ከግንባታ የተራረፉ ቁርጥራጭ ብረታ ብረት 200 ቶን ሽያጭ ጨረታ
ስስዚህ-
1. በዘርፉ የተሰማራችሁና በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣ የቫት ምዝገባ ሰርተፊኬት እንዲሁም የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥርየሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
2. በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወከሎቻቸው የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመከፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ) ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-10፡30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡30 – 6፡00) ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሽገ ኤምቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000.00 /አንድ መቶ ሽህ/ በባንክ የተመሰከረለት (CPO) ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
5. ተጫራች ለተጫረተው ዕቃ መነሻ ዋጋ መሰረት ለመግዛት በቂ አቅም መኖሩን ለማረጋገጥ የባንክስቴትመንት ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
6. ይህ ጨረታ እየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታ 15 ቀናት ከፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡
7. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 60 ቀናት ነው።
8. የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታው ዋጋ ጸንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለተከታታይ 60 ቀናት ነው፡፡
9. የዕቃው ርክክብ የሚፈፀመው አሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካ የሚገኝበት ማለትም ደቡብ ኢትዮጵያ ከልል ደቡብ ኦሞ ዞን ኃይል ውሃ ቀበሌ ነው::
10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
11. የጨረታው ሰነድ የሚሽጥበት የሚገባበትና የሚከፈትበት አድራሻ ቀጥሎ የተመለከተው ይሆናል።
አድራሻ፡- ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አዲስ አበባ ነው:: ለበለጠ መረጃ ይህን የስልከ ቁጥር መጠቀም ይቻላል 0991149485 /0940209464
የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ
