ብርሃን ባንክ አ.ማ ከባለእዳዎቹ ላይ ለሚፈልገው ገንዘብ በዋስትና የያዛቸውን እና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረትቶች በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እና በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሠረት ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ብርሃን ባንክ አ.ማ እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!
BERHAN BANK S.C
የሐራጅ ማስታወቂያ
ብርሃን ባንክ አ.ማ ከባለእዳዎቹ ላይ ለሚፈልገው ገንዘብ በዋስትና የያዛቸውን እና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረትቶች በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እና በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሠረት ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች በመገንዘብ ማክበር ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋውን የ1/4 (አንድ አራተኛ) (ሲፒኦ) በብርሃን ባንክ አ.ማ ስም ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን እንዳሸነፈ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ ንብረቱን መረከብ አለበት፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ይመለስላቸዋል፡፡
- የመኖሪያ ንግድ ቤቶቹ ጨረታ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ይከናወናል፡፡
- የጨረታ አሸናፊው በሚገዛው ንብረት ላይ የሚፈለግ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ግብር፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያዎች እና የሊዝ ክፍያዎች ይመለከተዋል፡፡
- መያዣ ሰጪዎች ሐራጁ በሚከናወንበት ቦታ ቀንና ሰዓት መገኘት ይችላሉ፡፡ ባይገኙ ግን ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
- በባንኩ ብድር መምሪያ መስፈርት መሰረት እና በተሰጠው ጊዜ ውስጥ የሚፈለግበትን ለሚያሟላ ተጫራች ባንኩ በከፊል ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡
- ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች በስራ ሰዓት ኘሮግራም አስይዞ ለመጐብኘት ይቻላል፡፡
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
የመኖሪያ እና ንግድ ቤቶች
ተ.ቁ |
የተበዳሪዉ ስም |
የመያዣ ሰጭዉ ስም |
መኖሪያ/ የንግድ ቤት የሚገኝበት አድራሻ |
የቦታው ስፋት በካሬ ሜትር |
የንብረቱ አገልግሎት |
የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር |
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
ጨረታዉ የሚካሄድበት ቀን እና ሰዓት፤ |
1. |
ያረጋል ይፍረደው መንግስቱ(ክሮስ ላንድ ኮንስትራክሽን) |
አዲስ ደስታ ተክለወልድ |
አ.አ ከተማ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 09 |
250 ካ.ሜ |
አፓርትመንት፣ ባር እና ሬስቶራንት |
LMK1111647572504246 |
84,800,000.00 |
ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-5፡30 |
2. |
ቴዎድሮስ ተሾመ |
ደረጀ አድማሱ |
አ.አ ከተማ ን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ አድራሻ የካዳስተር ብሎክ 12 |
150 ካ.ሜ |
መኖሪያ ቤት |
AM000081202457 |
10,600,000.00 |
ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-5፡30 |
3. |
ቴዎድሮስ ተሾመ |
ኢስት ጌት ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
አ.አ ከተማ ን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 01 |
500 ካ.ሜ |
ለተለያየ አገልግሎት |
AM000081203181 |
46,700,000.00 |
ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00-9፡30 |
4. |
ጌትነት መንግስት |
ጌትነት መንግስት |
እንጅባራ ከተማ 02 ቀበሌ |
175 ካ.ሜ |
መኖሪያ ቤት |
572/2014 |
2,900,000.00 |
ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-5፡30 |
5. |
ጌትነት መንግስት |
ጌትነት መንግስት |
እንጅባራ ከተማ 02 ቀበሌ |
175 ካ.ሜ |
ንግድ |
43/2010 |
8,000,000.00 |
ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00-9፡30 |
ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 011-6506900 እና 011-6506276 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
