Tender Detail

Tender Details

  • Company KK PRIVATE LIMITED COMPANY (ኬኬ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ)
  • Address ቃሊቲ ከቲሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል በላይ፣ መርካቶ ቅርንጫፍ ዲር (Dir) ህንጻ እና 5ኛ ፎቅ ቀጨኔ ቅርንጫፍ፡ ቀጨኔ አካባቢ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251 115 1590 15
  • Websitehttps://kkplcethiopia.et/aboutus.html
  • Deadline16 Jul 2026, 5:00 PM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price1000.00
  • opening date2026-07-17 10:00:00
  • Categories Rent , Land, House, Building And Warehouse Rent

ኬኬ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ ካስገነባቸው ዘመናዊ ሕንፃዎች መካከል የአፍሪካ ገበያ ማዕከል በሆነው ከመርካቶ በቅርብ ርቀት በሚገኘው በተለምዶ ጨው በረንዳ ተብሎ በሚጠራው እና በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ውስጥ ባለ 5 ወለል ዘመናዊ ህንፃ አጠናቆ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ሙሉ ሕንፃውን ለአንድ ተጫራች ማከራየት ይፈልጋል፡፡


ኬኬ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ

KK PRIVATE LIMITED COMPANY

 

የሕንፃ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ

 

ኬኬ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ ካስገነባቸው ዘመናዊ ሕንፃዎች መካከል የአፍሪካ ገበያ ማዕከል በሆነው ከመርካቶ በቅርብ ርቀት በሚገኘው በተለምዶ ጨው በረንዳ ተብሎ በሚጠራው እና በአዲስ ከተማ /ከተማ ወረዳ 6 ውስጥ ባለ 5 ወለል ዘመናዊ ህንፃ አጠናቆ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ሙሉ ሕንፃውን ለአንድ ተጫራች ማከራየት ይፈልጋል፡፡

ሕንፃው የውሃ፣ የኤሌትሪክ የኢንተርኔት ዝርጋታ የተሟላለት ከመሆኑም በላይ ለአካል ጉዳተኞች እና ለአቅመ ደካሞች ዘመናዊ ሊፍት የተገጠመለት ሲሆን የመኪና ማቆሚያ አያሳስቦት 50 በላይ መኪኖችን ማስተናገድ የሚችል የመኪና ፓርኪንግ ያካተተ ነው፡፡

ለሚከራዩት ሕንፃ ከስርቆት ስጋት ነፃ እንዲሆኑ ኬኬ በራሱ ወጪ አስተማማኝ 24 ሰዓት ጥበቃ እና ዘመናዊ ካሜራ አስገጥሟል፡፡

እናስ ምን ይጠብቃሉ? ይፍጠኑ ይህን እንከን የለሽ ዘመናዊ ሕንፃ ሳያመነቱ ይከራዩ፡፡ ሕንፃው ለባንክ አገልግሎት፣ ለኢንሹራንስ፣ ለገንዘብና ብድር ተቋማት እንዲሁም ለትምህርትና ለጤና አገልግሎት ምቹ በመሆኑ ፍላጎት ያላችሁ በጨረታው እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል፡፡

የጨረታ ስነዱን ለማግኘት ሕንፃው በተገነባበት ጨው በረንዳ በሚገኘው ቢሮአችን በመምጣት ለጨረታ ሰነዱ መግዣ የማይመለስ ብር አንድ ሺህ (1,000) ብር በመክፈል ሰነዱን ማግኘት ትችላላችሁ

ጨረታው ይሕ ማስታወቂያ ከወጣበት ወይም ከተነገረበት ከሰኔ 29 ቀን 2018 . ጀምሮ ለአስር ተከታታይ የስራ ቀናቶች ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን ጨረታው ሐምሌ 9 ቀን 2018 .. ምሽት 11 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በበነጋታው ሐም 10 ቀን 2018 .. ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 400 ሰዓት ይከፈታል::

ኬኬ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ተጨማሪ ማብራሪያ በጨረታ ሰነዱ ላይ ያገኛሉ።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0939-422324 / 0911- 248333 በስራ ሰዓት ብቻ ይደውሉ።

 

ኬኬ /የተ/የግል ኩባንያ

Save Tender