በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በሕገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስና የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች፣ ሞባይሎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችና ጌጣጌጥ እና አካላት፣ አልባሳት፣ ጫማዎች፣ ጊርቦከስ እና ሌሎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ መሸጥ ይፈልጋል።
በጉምሩክ ኮሚሽን የአ/አ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ልዩ ልዩ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ እና
በሐራጅ ጨረታ ቁጥር 01/2019፣02/2019፣03/2019:04/2019፣05/2019፣06/2019፣07/2019:08/2019 እና 09/2019
የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዜያት የጉምሩከ ሥነ-ሥርዓት ባለመፈጸሙ ምክንያት እና በሕገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስና የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች፣ ሞባይሎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችና ጌጣጌጥ እና አካላት፣ አልባሳት፣ ጫማዎች፣ ጊርቦከስ እና ሌሎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ እና በሐራጅ ጨረታ ቁጥር 01/2019 በቀን 2/11/2018ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 02/2019 በቀን 6/11/2018ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 03/2019 በቀን 09/11/2018ዓ.ምጨረታ ቁጥር 04/2019 በቀን 13/11/2018ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 05/2019 በቀን 16/11/2018ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 06/2019 በቀን 20/11/2018ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 07/2019 በቀን 23/11/2018 ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 08/2019 በቀን 27/11/2018ዓ.ም እና ጨረታ ቁጥር 09/2019 በቀን 30/11/2018ዓ.ም በመሆኑ የቀጣይ 2019 በጀት ዓመት ዕቅድ በተፈለገው መጠን ለማሳካት ለሁሉም ተደራሽነት ባለው መልኩ በጋዜጣ ማስታወቂያ እንዲወጣልን እየጠየቅን ዝርዝር መረጃ ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 1-14 እንገልፃለን፡፡
በመሆኑም:-
1. በቅ/ጽ/ቤቱ ለሚካሄደው ጨረታ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የተከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. ማንኛውም የግልጽ ጨረታ ተጫራች ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ ዘወትርበሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 - 8፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 - 11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡ 00 - 6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ገርጂ ጉምሩክ መጋዘን ቅጥር ግቢየውርስ ዕቃዎች አወጋገድ ቡድን በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላል፡፡
3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና (CPO) CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA AIRPORT CUSTOM BRANCH OFFICE ስም ማሠራት ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ናሙና በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩከ ካርጎ መጋዘን እና ገርጂ መጋዘን ሐምሌ 2/2018 ዓ/ም፣ ሐምሌ 6/2018 ዓ.ም ሐምሌ 9/2018ዓ.ም፣ ሐምሌ 13/2018 ዒ.ም፣ ሐምሌ 16/2018 ዓ/ም፤ ሐምሌ 20/2018 ዓ/ም፣ ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ተዘግቶ በዛው ቀን በ8፡15 የሚከፈት ይሆናል፡፡
5. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ለጨረታው የሚሰጡትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዘው በቀረቡት ቅጾች መሠረት ለመረጡት የዕቃዎች ኮድ የተሰጠ ዋጋ፥ የተጫራቾች ስም አድራሻ፣ ፊርማና የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) እና ከላይ በተ.ቁ 1 የተገለጹትን ሰነዶች ኮፒበታሸገ ኤንቨሎፕ ላይ በመፈረም አዲስ አበባ ኤርፖርት ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ገርጂ የውርስ ዕቃዎችአወጋገድ ቡድን ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
6. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነዱ የሰጠውን መግዣ ዋጋናመግለጫ መለውጥና ማሻሻል አይችልም፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች የሰጠውን የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ የጨረታውውጤት እስከሚታወቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
8. የጨረታው አሸናፊዎች ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ በ05 (አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለባቸው::
9. ከላይ በተ/ቁ 8 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረገ እና ንብረቱን ተረከቦያልወሰደ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
1. በተራ ቁጥር 01 - 09 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም በሐራጅ ጨረታ ቁጥር 01/2019
2. በቀን 2/1/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 02/2019 በቀን 6/11/2018 ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 03/2019
3. በቀን 9/1/2018 ዓ.ም፡ጨረታ ቁጥር 04/2019 በቀን 13/1/2018 ዓ.ም፤ ጨረታ ቁጥር 05/2019
4. በቀን 16/1/2018 ዓ.ም፡ ጨረታ ቁጥር 06/2019 በቀን 20/11/2018 ዓ.ም ፣ጨረታ ቁጥር 07/2019
5. በቀን 23/1/2018 ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 08/2019 በቀን 27/1/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 09/2019
6. በቀን 30/11/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የምናካሄድ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ እያሳወቅን፣ የዕቃዎችን ናሙና በአዲስ አበባ ኤርፖርትጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ገርጂ እና ካርጎ ውርስ መጋዘን በመገኘት መመልከት ይቻላል፡፡
10. በሐራጅ ጨረታ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100.00 (አንድ መቶ) ለየዘርፉ CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA AIRPORT CUSTOM BRANCHOFFICE ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
11. ለጨረታ የቀረቡት የዕቃዎች ዋጋ ከቫት በፊት የተሰጠ መሆኑ እናሳውቃለን፡፡
12. ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች በተናጠል ሳይሆን ለጨረታው ሰነዱ በተሰጠ ኮድ ቁጥር ብቻ የሚሸጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
13. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
14. በቅ/ጽ/ቤት ደረጃ እየተካሄደ ያለውን የጨረታ አድማስ ለማስፋት፣ ፈጣን የዕቃዎች ማስወገድ ሥራ በማከናወን እና ገቢን በወቅቱ ለመሰብሰብ እንዲቻል ጨረታዎችን በወረቀት አልባ (Online) አሠራር ለማስኬድ ከአክሽን ኢትዮጵያ ኢማ ጋር ለመሥራት በመታሰቡ ዘወትር ሐሙስ የሚካሄደውን ግልፅ ጨረታ በቀጥታ ሙሉ በሙሉ በአክሽን ኢትዮጵያ ኢማ በወረቀት አልባ (Online) የሚካሄድ መሆኑን እናሳውቃለን፤
15. የኦከሽን ኢትዮጵያ ኢማ መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር +251905115511 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፤
16. በጉምሩክ ኮሚሽን ክፍያ የሚታሰብ አንድ ጋዜጣ ለቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን እንዲሰጠንእንጠይቃለን፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ቦሌ ኤርፖርት በስልክ ቁጥር 011 668 45 37 እና 011 668 41 93 ደውለው ይጠይቁ።
በጉምሩክ ኮሚሽን የአ/አ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
