Tender Detail

Tender Details


የኢትዮጵያ እየር መንገድ ግሩፕ በአምስት የሀገር ውስጥ ኤርፖርቶች (ደብረ ማርቆስ፣ ሚዛን አማን፥ ነገሌ ቦረና፣ ጎሬ ሙቱ፤ ወላይታ ሶዶ) የሚገኝ ለአውሮፕላን ነዳጅ ዴፖ ግንባታና ነዳጅ አቅርቦት አገልግሎት የሚሆን ከፍት ቦታ በረጅም ጊዜ የኮንትራት ውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡


የአውሮፕላን ነዳጅ ዴፖ ግንባታ እና የነዳጅ አቅርቦት ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር:-SSNT-T624

 

የኢትዮጵያ እየር መንገድ ግሩፕ በአምስት የሀገር ውስጥ ኤርፖርቶች (ደብረ ማርቆስ፣ ሚዛን አማን፥ ነገሌ ቦረና፣ ጎሬ ሙቱ፤ ወላይታ ሶዶ) የሚገኝ ለአውሮፕላን ነዳጅ ዴፖ ግንባታና ነዳጅ አቅርቦት አገልግሎት የሚሆን ከፍት ቦታ በረጅም ጊዜ የኮንትራት ውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፦

1.     ህጋዊና የታደሰ የነዳጅ አቅርቦት ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ ታከስ ምዝገባ የምስከር ወረቀት ያላቸው: በኢትዮጵያ በነዳጅና በዘይት አቅርቦት የሶስት ዓመት እና ከዛ በላይ ልምድ ያላቸው እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው ፤በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ ማንኛውም ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

2.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ረቡዕ, ሐምሌ 29 ቀን 2018 .. ከቀኑ 9:00 ሰዓት ባሉት ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T624 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የነቢ ደረሰኝ (Deposit Slip) ቅጂውን (scan copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡

3.     በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት ለእያንዳንዱ ቦታ የጨረታ ማስከበሪያ ብር100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ 120 ቀናት የሚያገለግል በባንክበተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለበት ፡፡ ከኢንሹራንስ እና ቅድመ ሁኔታ ያለው ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።

4.     ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋናውን እና ቅጂውን ቴክኒካል ሰነድ፣ ዋናውን እና ቅጂውን ፋይናንሻል ሰነድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ለየብቻ በማሸግ በኢትዮጵያ እየርመንገድ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤት ውስጥ በሚገኘው ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል ረቡዕ, ሐምሌ 29 ቀን 2018 .. እስከ ከቀኑ 9:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው:: ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን 930 ሰዓት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ መከፈቻ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ:-

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

ቦሌ አለም አቀፍ እየር ማረፊያ

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል

ያዕቆብ መስቀላ: በስልክ ቁጥር፡ +251-115-17-80-25 በመደወል መጠየቅ ይቻላል::

.ሜ.ል Yaikob@ethiopianairlines.com

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

Save Tender